#ቀጥታ_live
Автор: ቤተ ሠናያተ Bete Senayate
Загружено: 2026-01-18
Просмотров: 7947
#ከተራ_ketera #ephipheny_celebration #Timket_in_ethiopia
ከተራ ! እንኳን አደረሳችሁ
"ከተራ” በአጼ ይኩኑ አምላክ መንግስት የተጀመረው እና በአጼ ገብረ መስቀል መንግስት በአደባባይ እንዲከበር የታወጀው የጥምቀት ክብረ በዓል ከመከበሩ አንድ ቀን ቀደም ብሎ የሚከበር ራሱን የቻለ ሰፋ ያለ እምነታዊ ታሪክ ያለው በጥንታዊት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምዕመናን በደመቀ ሁኔታ የሚከበር ክብረ በዓል ነው ።
“ ከተራ” ከተረ ከሚለው የግዕዝ ቃል የተወረሰ ሲሆን አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ “ከተረ” ፣ ወሃ ገደበ፣ ውሃ አገደ፣ ውሃ ዘጋ ውሃ ቋጠር ውሃ ያዘ በማለት ወደ አማርኛ ተርጉመውታል ።
ታዲያ በየዓመቱ ጥር 10 የጥምቀት ዋዜማ ዕለት ጀምበር ከመጥለቋ በፊት ቀደም ብለው የቤት ክህነት አገልጋዮች ተሰባስበው ጊዜዊ ውሃ ማጠራቀሚያ ገንዳ በመቆፈር ወይም በአቅራቢያቸው ያለውን ጅረት በመገደብ ለሚቀጥለው ጥር 11 የጥምቀትን ክብረ በዓል ለማክበር የሚሰበሰቡት ምዕመናን እንዲጠመቁ የመጠመቂያ ስፋራ የሚያዘጋጁበት ዕለት ነው።
በተጨማሪ በአቅራቢያ የሚገኙት ቤተክርስቲያናት ተሰብስበው ከዚሁ ከተቆፈረው ገንዳ ወይም ከተገደበው ጅረት አጠገብ ዳስ ወይም ድንኳን ጥለው ታቦቶቻቸውን ያሳድራሉ።
ቅዱሳን አባቶቻችንም በየዓመቱ በከተራ ዕለት በዚሁ በአዘጋጁት የመጠመቂያ ስፋራ አጠገብ በጣሉት ጊዚያዊ ዳስ ወይም ድንኳን ውስጥ አንድ ላይ ተሰባስበው እየጸለዩ በማደር እግዚአብሔር ለነብዩ ሙሴ “የታቦት መኖር የእኔ ከአናንተ ጋር የመኖሬ ምልክት ነው” ብሎ የገለጸለትን ቃል ይፈጽማሉ።
Ketera is the eve of the Timket (Ethiopian Epiphany) celebration and marks the spiritual preparation for the baptism ceremony.
On this day, the sacred Tabots (replicas of the Ark of the Covenant) are ceremonially taken from churches to nearby bodies of water.
Priests, deacons, and thousands of faithful followers join the procession with spiritual chants, prayers, traditional drums, and white garments, expressing deep faith and devotion.
Ketera symbolizes spiritual readiness, unity, and reverence, paving the way for the Timket celebration the following day.
🔴 Watch Ketera LIVE from Ethiopia
🙏 Experience Ethiopian Orthodox tradition and spirituality
👉 Subscribe • Like • Share
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: