ሶዞ አኮስቲክ ባንድ - ዜማ || SOZO Acoustic Band - Zema (Official Audio)
Автор: Senfam Music
Загружено: 2025-06-25
Просмотров: 3705
Lyrics:
ዜማ
የክረምት ደመና በኖ ወጣሁ ለዜማ
የበልጉም ወራትም አልፎ ነጎደ በቃ
ከተሰቀለበት ቦታ ወርዶ በገናዬ
ድምፄንም ላሰማ በምሥጋናዬ፡፡
የበልጉ ወር ጭጋጉ ጽልመቱ ጉሙ አለፈ
ከዓለት ሁሉ ውኃ ፈሰሰ
የሰማዩ ጉም በኖ መስኩ አመልማሎ ሆነ
ከምድር ዙሪያ ግርዶሽ በነነ፡፡
ዜማ ላሰማ
ክረምቱ ሄደ ወጣሁ ለዜማ
ዜማ ሳሰማ
ሄደ ጨለማ
ብራ ቀን ሆነ ነግቶ ዛሬማ፡፡
የምድር አበቦች ፈኩ በየሜዳው ሁሉ
እጅግ አማሩ ውበት ለበሱ
የባሕር ጅረቶች ድፍርሳቸው ሁሉ ጠራ
ደመናን ቀዶ ብርሃን በራ፡፡
ዜማ ላሰማ
ክረምቱ ሄደ ወጣሁ ለዜማ
ሄደ ጨለማ
ብራ ቀን ሆነ ነግቶ ዛሬማ፡፡
የተራሮች አናት ልምላሜን ለብሰው ታዩ
በመረዋ ድምጽ ወፎች አዜሙ
የምድር መዓዛ ያልባስጥሮስ ሽቶ ሆነ
የሚያውድ ጠረን እጅግ ገነነ
የሚያውድ ጠረን እጅግ ገነነ፡፡
ዜማ ላሰማ
ክረምቱ ሄደ ወጣሁ ለዜማ
ሄደ ጨለማ
ብራ ቀን ሆነ ነግቶ ዛሬማ፡፡
የበልጉ ወር ጭጋጉ ጽልመቱ ጉሙ አለፈ
ከዓለት ሁሉ ውኃ ፈሰሰ
የሰማዩ ጉም በኖ መስኩ አመልማሎ ሆነ
ከምድር ዙሪያ ግርዶሽ በነነ፡፡
ዜማ ላሰማ
ክረምቱ ሄደ ወጣሁ ለዜማ
ሄደ ጨለማ
ብራ ቀን ሆነ ነግቶ ዛሬማ፡፡
ክረምት ሄደ በጋው መጣ
ዜማ ወጣ።
አዎ
© Senfam Production publishing
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: