Популярное

Музыка Кино и Анимация Автомобили Животные Спорт Путешествия Игры Юмор

Интересные видео

2025 Сериалы Трейлеры Новости Как сделать Видеоуроки Diy своими руками

Топ запросов

смотреть а4 schoolboy runaway турецкий сериал смотреть мультфильмы эдисон
dTub
Скачать

ሰኔ 12 የቅዱስ ሚካኤል በዓል ወረብ | Sene Mikael Wereb | በመምህር ፍሬ ስብሐት መንገሻ | አ.አ. | መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ

Автор: ማኅሌት Mahlet

Загружено: 2020-06-18

Просмотров: 10170

Описание:

#እንኳን_ለቅዱስ_ሚካኤል_በዓል_በሰላም_አደረሳችሁ፡፡
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
እነሆ ይህች ዕለት ለቅዱሳን መላእክት አለቃቸው የሆነ፣ የስሙ ትርጓሜ "ማን እንደ አምላክ" የሆነ፣ የመልአከ ምሕረት ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል በዓለ ሢመት ዓመታዊ መታሰቢያ ናት፡፡ ፈጣሬ ዓለማት ልዑል እግዚአብሔር ዕፁብ ድንቅ በሆነ በማይመረመር ጥበብ ፍጥረታትን ከፈጠረባቸው ስድስት ዕለታት በመጀመርያዪቱ ዕለት በእሑድ መላእክትን ከፈጠራቸው በኋላ በተሰጣቸው አእምሮ ይመራመሩ ዘንድ ተሠወራቸው፡፡ ታድያ ይህን ጊዜ በመላእክት ዓለም ሁከት ተነሣ፤ ማን እንደፈጠራቸው አላወቁምና፡፡ ሳጥናኤልም ከወደ በላዩ ተመለከተ፤ ከእርሱ በላይ የሆነ ማንንም አላገኘም፡፡ ወደ ታችም ተመለከተ፤ እልፍ አእላፋት መላእክት ፈጣሪያቸው ማን እንደሆነ እየጠየቁ ነው፡፡ ይህን ጊዜ ነበር "እኔ ፈጠርኋችሁ" ብሎ የመጀመርያውን የሐሰት ንግግር የተናገረው፡፡ በሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል "ባለንበት እንጽና" ድንቅ ቃል ዘጠና ዘጠኙ ነገደ መላእክት ጸንተው ሲቆሙ በሳጥናኤል ነገድ ግን ክሕደት በርክቶ ነበር፡፡ ታዲያ ይህች ቀን ቅዱስ ሚካኤል ዲያቢሎስን ተዋግቶ ያሸነፈባት፣ የማይገባውን አምላክነትን ሽቶ በወደቀው በከሐዲው ዲያቢሎስ ምትክ ከወገኖቹ ከመላእክት ሁሉ በላይ ሆኖ በሁሉ ቅዱሳን መላእክት ላይ ከልዑል እግዚአብሔር ከክብሩና ከገናናነቱ ጋር ሹመትን ያገኘባት ታላቅ ዕለት ናት፡፡ ሹመቱም በአንድ ነገድ ላይ ብቻ አይደለም፤ በሁሉ የመላእክት ነገድ ላይ እንጂ፡፡ እርሱም በመንፈሳዊ ሕይወት የደከሙትን የሚያበረታ፣ አርምሞ ትዕግሥትን የሚወድድ፣ ለፍጥረታት ሁሉ የሚራዳና የሚያዝን፣ የምሕረትና የመዳኛ፣ የሰላም መልአክ ትሑትና ርኅሩኅ ነው፡፡ ዳግመኛም ይህች ዕለት ንዕድ ክብርት የሆነች ቅድስት አፎምያ የዕረፍቷ መታሰቢያ ናት፡፡ ቅድስት አፎምያ አንድ ሃይማኖቱ የቀና እግዚአብሔርንም የሚፈራ ስሙ አስተራኒቆስ የተባለ ታላቅ መኰንን ሚስት ነበረች፡፡ ባሏ አስተራኒቆስ ለምስኪናን ምጽዋትን የሚሰጥ፣ በየወሩም ሦስት ጊዜ በዓላትን የሚያከብር ደግ ሰው ነበር፡፡ እነዚህም በዓላት ወር በገባ በ፲፪ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል፣ በ፳፩ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም እና በ፳፱ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደቱ መታሰቢያ በዓላት ናቸው፡፡ ታዲያ በአንድ ወቅት ይህ ሰው ታመመ፤ የሚሞትበት ጊዜም ደረሰ፡፡ ይህን ጊዜ ሚስቱን አፎምያን እርሱ በሕይወት ዘመኑ ያደርገው የነበረውን መመጽወትን እንዳታስቀር ነገራት፡፡ የበዓላቱን መታሰቢያም አታስታጕል ዘንድ አደራ አላት፡፡ እርሷም ባሏን፣ በቤቷ አኑራ ከሰይጣን ፈተና ትከላከልበት ዘንድ የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል አሥሎ ይሰጣት ዘንድ ጠየቀችው፤ እርሱም ይህን ካደረገላት በኋላ ዐረፈ፡፡ ከባሏ ማረፍ በኋላ ቅድስት አፎምያ እርሱ ይሠራው ከነበረው በጎ ሥራ ሁሉ አንዳች ሳታጓድል እየሠራች በሃይማኖት ጸንታ ትኖር ጀመር፡፡ የክፋት አባት የሆነው ዲያቢሎስም በጎ ምግባሯን ባየ ጊዜ በቅንዓት ተነሣባት፤ በብዙም ፈተናት፡፡ በመበለት መነኰሳይት ተመስሎ እየመጣ በጣም እንደሚያዝንላት፣ ዕድሜዋ ሳያልቅ ገንዘቧም በምጽዋት ከማለቁ በፊት ብታገባና ልጆች ወልዳ ብትኖር እንደሚሻል ይመክራት ጀመር፡፡ ቀጥሎም፤ "ባልሽ እንደሆነ መንግሥተ ሰማያትን ወርሷል ምጽዋትን አይፈልግም፡፡" ብሎ ሊያሰናክላት ሞከረ፡፡ እርሷ ግን፤ "ከእንግዲህ ከሌላ ወንድ ጋር ላልገናኝ ለእግዚአብሔር የመሐላ ቃሌን ሰጥቻለሁና አላደርገውም፡፡" ብላ መለሰች፡፡ "ርግቦችና ቁራዎች ስንኳ ባላቸው ከሞተ ሌላ ባል አያውቁም፡፡ በአርአያ እግዚአብሔር ለተፈጠሩ ሰዎችማ ይህን ማድረግ እንዴት ይገባል?" አለችው፡፡ ምንም ያህል ቢጥርም እንኳን ነገሩን እንዳልተቀበለችው ባየ ጊዜ መልኩን ለውጦ ዛሬ ባይቻለውም እንኳን በሌላ ቀን መጥቶ ሃሳቡን እንድትቀበል እንደሚያደርጋት በመናገር ጮኸ፤ በቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ኀፍረትን አከናንባ አዋርዳ አጠፋችው፡፡ በሰኔ ፲፪ በሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል ቀን ዲያቢሎስ ዳግመኛ ሊፈትናት ብርሃናዊ መልአክ መስሎ የብረት ዘንግ ይዞ በሌሊት ወደ እርሷ መጣ፡፡ ስለ በጎ ሥራዎችዋ ስለ መልካምነቷ ከክፉ እንዲጠብቃት ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ እንደመጣ ነገራት፡፡ ስሙን ብትጠይቀው የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነ ዋሽቶ ነገራት፡፡ "እነሆ ገንዘብሽን በምጽዋት ማባከንሽን ትተሸ ከምእመናን ወገን ለአንዱ ሚስት ትሆኚ ዘንድ እግዚአብሔር ወደ አንቺ ልኮኛል፡፡ በዚህም ላይ ያለ ባል የምትኖር ሴት መቅዘፊያ እንደሌላት ወይም መልሕቅዋ እንደተቆረጠ መርከብ መሆንዋን ዕወቂ፡፡" አላት፡፡ ከብሉይ መጻሕፍት እነ አብርሃም፣ ይስሐቅ፣ ያዕቆብ ፣ ዳዊትን እያነሣ ያገቡ ነገር ግን የእግዚአብሔር ባለሟሎች የነበሩ መሆናቸውን ጠቅሶ ማግባት እንዳለባት ነገራት፡፡ ቅድስት አፎምያም መልሳ በእውነት የእግዚአብሔር መልአክ ከሆነ የመታወቂያው ምልክት የሚሆን ትእምርተ መስቀሉ ወደየት እንዳለ ጠየቀችው፡፡ እርሱም፤ "በእኛ በመላእክት ዘንድ እንዲህ ያለ ምልክት የለም፡፡" አላት፡፡ በእጅጉ ስለተጠራጠረችው ባሏ ከመሞቱ በፊት አሠርቶ የሰጣትን የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል ልታመጣ ወደ ሥዕል ቤቷ ሔደች፡፡ ይህን ጊዜ ዲያቢሎስ መልኩ ተለወጠ፤ ዘልሎም አነቃት፡፡ ቅድስት አፎምያ ወደ ቅዱስ ሚካኤል እንዲያድናት እየጮኸች ለመነች፡፡ ለመልካም ሥራ የሚፋጠን መልአከ ኃይል ቅዱስ ሚካኤልም መጥቶ አዳናት፡፡ ሰይጣኑንም በብዙ ሥቃይ አሠቃየው፡፡ ሰይጣኑም እግዚአብሔር የሰጠው ዘመኑ ሳይፈጸም አያጠፋው ዘንድ ቅዱስ ሚካኤልን ተማፀነው፤ ያን ጊዜም ተወው፡፡ ከዚህ በኋላም የቅድስት አፎምያ የዕረፍቷ ቀን ደርሷልና ቅዱስ ሚካኤል ሔዳ ቤቷን ታዘጋጅ ዘንድ ነገራት፡፡ "በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ትለያለሽ፡፡ እነሆ እግዚአብሔርም ዐይን ያላየውን ጆሮ ያልሰማውን ልቡና ያላሰበውን ዋጋሽን አዘጋጅቶልሻል፡፡" ብሎ ከነገራት በኋላ ሰላምታ ሰጥቷት ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ እርሷም ለበዓሉ የሚያስፈልገውን ከአዘጋጀች በኋላ ወደ ኤጲስ ቆጶሱ እና ካህናቱ ዘንድ መልእክተኛ ላከች፤ ቀጥሎም በእነርሱ እጅ ለነዳያንና ለችግረኞች ምጽዋትን ይሰጡላት ዘንድ ገንዘብን ሰጠች፡፡ ከዚህም በኋላ የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል በደረቷ እና በፊቷ ላይ አድርጋ ወደ እግዚአብሔር እየጸለየች የቅዱስ ሚካኤል በዓል በሚከበርበት ዕለት በሰኔ ፲፪ ቀን በክብር ዐረፈች፡፡ አምላከ አማልክት ልዑል እግዚአብሔር ከክፉ ዲያቢሎስ እጅ ያስጥላት ዘንድ ቅዱስ ሚካኤልን ወደ ቅድስት አፎምያ እንደላከ እኛንም በፈተናዎቻችን ሁሉ ይረዳን ዘንድ ከቅዱስ ሚካኤል ረድኤት በረከት ይክፈለን፡፡ አሜን፡፡ ይቆየን……. ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ሰኔ 12 የቅዱስ ሚካኤል በዓል ወረብ | Sene Mikael Wereb | በመምህር ፍሬ ስብሐት መንገሻ | አ.አ. | መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ

Поделиться в:

Доступные форматы для скачивания:

Скачать видео mp4

  • Информация по загрузке:

Скачать аудио mp3

Похожие видео

ግንቦት 21 ደብረ ምጥማቅ ማርያም ወረብ|Ginbot 21 Debre Mitmaq Wereb|በመምህር ፍሬ ስብሐት መንገሻ|አ.አ| መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ

ግንቦት 21 ደብረ ምጥማቅ ማርያም ወረብ|Ginbot 21 Debre Mitmaq Wereb|በመምህር ፍሬ ስብሐት መንገሻ|አ.አ| መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ

የአቡነ ገሪማ በዓል ወረብ | Abune Gerima Beal Wereb | በመምህር ፍሬስብሐት መንገሻ | አ.አ

የአቡነ ገሪማ በዓል ወረብ | Abune Gerima Beal Wereb | በመምህር ፍሬስብሐት መንገሻ | አ.አ

🔴NEW ቅዱስ ሚካኤል በዓል መዝሙሮች [Kidus Mikael Mezmur] መዝሙር ስብስብ @ritin-tube

🔴NEW ቅዱስ ሚካኤል በዓል መዝሙሮች [Kidus Mikael Mezmur] መዝሙር ስብስብ @ritin-tube

🛑ጀግናው ተሰዋ/ጥር/18/2018/Ethiopianews TodayJanuary/26/2026 Breaking News.

🛑ጀግናው ተሰዋ/ጥር/18/2018/Ethiopianews TodayJanuary/26/2026 Breaking News.

ክፍል አንድ ወረብ ዘሰኔ ሚካኤል  ቅኝት ጸናጽል ወቸብቸቦ በመምህር ልሳነ ወርቅ ሞላ

ክፍል አንድ ወረብ ዘሰኔ ሚካኤል ቅኝት ጸናጽል ወቸብቸቦ በመምህር ልሳነ ወርቅ ሞላ

የአየር ኃይሉ ጉዶችና የጀኔራሉ ሚስት  ፣ ቅቤ ነጋዴው ጀኔራልና የተገደሉት ፓይለቶች|ETHIO FORUM

የአየር ኃይሉ ጉዶችና የጀኔራሉ ሚስት ፣ ቅቤ ነጋዴው ጀኔራልና የተገደሉት ፓይለቶች|ETHIO FORUM

"ቅዱስ ሚካኤል" - ዘማሪ ገብረዮሐንስ ገብረፃድቅ | ቤተ ቅኔ - Beta Qene

በዓለ ርዕሰ ዐውደ ዓመት ዮሐንስ ወቅዱስ ራጉኤል ወረብ | Ye Addis Amet ena  ye Kidus Raguel Wereb | በመምሕር ፍሬስብሐት መንገሻ

በዓለ ርዕሰ ዐውደ ዓመት ዮሐንስ ወቅዱስ ራጉኤል ወረብ | Ye Addis Amet ena ye Kidus Raguel Wereb | በመምሕር ፍሬስብሐት መንገሻ

ሦተኛው ቀን ማጠቃለያ  // የተዘረጉ የበረከት እጆች // የዋልድባ መነኮሳት አባቶች ጥሪ // ቆይታ ከዘመዴ ጋር #ethiobeteseb

ሦተኛው ቀን ማጠቃለያ // የተዘረጉ የበረከት እጆች // የዋልድባ መነኮሳት አባቶች ጥሪ // ቆይታ ከዘመዴ ጋር #ethiobeteseb

ግንቦት 12 የአቡነ ተክለሐይማኖት ፍልሰተ አጽም ክብረ በዓል ወረብ| Ginbot 12 Wereb| በመምህር ፍሬ ስብሐት | አ.አ | መናገሻ ገነተ ጽጌ

ግንቦት 12 የአቡነ ተክለሐይማኖት ፍልሰተ አጽም ክብረ በዓል ወረብ| Ginbot 12 Wereb| በመምህር ፍሬ ስብሐት | አ.አ | መናገሻ ገነተ ጽጌ

አንተኑ ሚካኤል ወረብ Antenu mikael wereb #ወረብ #አጫብር

አንተኑ ሚካኤል ወረብ Antenu mikael wereb #ወረብ #አጫብር

ሰበር ዜና:- ህወሓት በከተከዜ ግንባር ውጊያ ከፈተ!በከተማው የሌሊት ኦፕሬሽን ተፈጸመ!ካምፕ ተመታ!በ4 ግንባሮች ኃይል ተንቀሳቀሰ!አፀፋ ተሰጠ!

ሰበር ዜና:- ህወሓት በከተከዜ ግንባር ውጊያ ከፈተ!በከተማው የሌሊት ኦፕሬሽን ተፈጸመ!ካምፕ ተመታ!በ4 ግንባሮች ኃይል ተንቀሳቀሰ!አፀፋ ተሰጠ!

ዓይኑ ዘርግብ ልብሱ ዘመብረቅ ሩፋኤል ሐመልማለ ወርቅ | ወረብ ዘጳጉሜ ቅዱስ ሩፋኤል | Pagumen Rufael Wereb

ዓይኑ ዘርግብ ልብሱ ዘመብረቅ ሩፋኤል ሐመልማለ ወርቅ | ወረብ ዘጳጉሜ ቅዱስ ሩፋኤል | Pagumen Rufael Wereb

የመስከረም 1 ወረብ በመምህር ኢያቄም ታደሰ የመ/ገ/ጽ/ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን አገልጋይ YeMeskerem 1 wereb

የመስከረም 1 ወረብ በመምህር ኢያቄም ታደሰ የመ/ገ/ጽ/ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን አገልጋይ YeMeskerem 1 wereb

ድርሳነ ሚካኤል ሰኔ አማርኛ | Drsane Mikael | ethiopian orthodox tewahedo | @ancientethiopia

ድርሳነ ሚካኤል ሰኔ አማርኛ | Drsane Mikael | ethiopian orthodox tewahedo | @ancientethiopia

የሐምሌ 19 የቅዱስ ገብርኤል የቅዱስ ቂርቆስ እና የቅድስት እየሉጣ በዓል ወረብ | Hamle 19 Wereb | በመምህር ፍሬስብሐት መንገሻ | አ.አ

የሐምሌ 19 የቅዱስ ገብርኤል የቅዱስ ቂርቆስ እና የቅድስት እየሉጣ በዓል ወረብ | Hamle 19 Wereb | በመምህር ፍሬስብሐት መንገሻ | አ.አ

ለዛቲ ቤት ሐነጻ ወልድ ወፈጸማ መንፈስ ቅዱስ በጎንደር

ለዛቲ ቤት ሐነጻ ወልድ ወፈጸማ መንፈስ ቅዱስ በጎንደር

ሰበር ዜና ፣ ህወሓት ብልፅግናን አስጠነቀቀ ...ይበቃል ትግስታችን አልቃል ፣የTDF ቃል አቀባይ ለብልፅግና ማስጠንቀቂያ ፣የአሜሪካ በረዶ ሰዉ እየገደለ ነዉ

ሰበር ዜና ፣ ህወሓት ብልፅግናን አስጠነቀቀ ...ይበቃል ትግስታችን አልቃል ፣የTDF ቃል አቀባይ ለብልፅግና ማስጠንቀቂያ ፣የአሜሪካ በረዶ ሰዉ እየገደለ ነዉ

ሰኔ 21 በዓለ ህንጸተ ቤታ ለማርያም ወረብ| Sene 21 Wereb | በመምህር ፍሬ ስብሐት | አ.አ | መናገሻ ገነተ ጽጌ

ሰኔ 21 በዓለ ህንጸተ ቤታ ለማርያም ወረብ| Sene 21 Wereb | በመምህር ፍሬ ስብሐት | አ.አ | መናገሻ ገነተ ጽጌ

የሐምሌ 22 የቅዱስ ዑርኤል በዓል ወረብ | Hamle 22 Wereb | በመምህር ፍሬስብሐት መንገሻ | አ.አ

የሐምሌ 22 የቅዱስ ዑርኤል በዓል ወረብ | Hamle 22 Wereb | በመምህር ፍሬስብሐት መንገሻ | አ.አ

© 2025 dtub. Все права защищены.



  • Контакты
  • О нас
  • Политика конфиденциальности



Контакты для правообладателей: infodtube@gmail.com