lየማይፀና ውል! | ውል በህግ ፊት የማይፀናው (ፈራሽ የሚሆነው) መቼ ነው?
Автор: Law tube_የሕግ ቻናል
Загружено: 2025-12-20
Просмотров: 305
ውል በሁለት ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ ወገኖች መካከል የሚደረግ ግዴታን የሚጥል ስምምነት ነው። ነገር ግን እያንዳንዱ ስምምነት በህግ ፊት "ውል" ተብሎ አይወሰድም፤ ወይም ደግሞ በህግ ሊያስከስስ የሚችል ጥንካሬ ላይኖረው ይችላል።
በዚህ ቪዲዮ ውል በህግ ፊት የማይፀናባቸውን (Invalid/Void contracts) ዋና ዋና ምክንያቶች በኢትዮጵያ የፍትሐ ብሔር ህግ መሰረት በዝርዝር እንመለከታለን።
በቪዲዮው የተካተቱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
• የውል ተዋዋይ ወገኖች ብቃት፦ እድሜያቸው ለውል ያልደረሰ ወይም በአእምሮ ህመም ምክንያት ውል የመዋዋል ብቃት የሌላቸው ሰዎች የሚገቡት ውል ምን ይሆናል?
• ነፃ ፈቃድ (Consent)፦ ውል የተፈረመው በማስገደድ፣ በስህተት ወይም በማታለል ከሆነ ውጤቱ ምንድነው?
• የውሉ ዓላማ (Object)፦ የውሉ ዓላማ በህግ የተከለከለ፣ ከሞራል ውጭ የሆነ ወይም የማይቻል ከሆነ ውሉ ይፀናል?
• የፎርም ወይም የቅርፅ መስፈርት (Form)፦ በፅሁፍ መደረግ ያለባቸው ውሎች በቃል ቢደረጉ ውጤታቸው ምንድነው? (ለምሳሌ፦ የቤት ሽያጭ፣ የብድር ውል...)
ይህ ቪዲዮ ስለ ውል መሰረታዊ ግንዛቤ እንዲኖራችሁና ከመጭበርበር እንድትጠበቁ ይረዳችኋል።
🔔 ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ!
👉 / @eysehen1
ቪዲዮው ጠቃሚ ሆኖ ካገኙት Like በማድረግ ለሌሎች እንዲደርስ ያግዙ። ጥያቄ ካላችሁ በኮሜንት መስጫው ላይ አስቀምጡልኝ።
#ውል #የማይፀናው_ውል #EthiopianLaw #ContractLaw #ህግ #የኢትዮጵያህግ #LegalAdvice #LegalEducation #BusinessLaw #Ethiopia
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: