Популярное

Музыка Кино и Анимация Автомобили Животные Спорт Путешествия Игры Юмор

Интересные видео

2025 Сериалы Трейлеры Новости Как сделать Видеоуроки Diy своими руками

Топ запросов

смотреть а4 schoolboy runaway турецкий сериал смотреть мультфильмы эдисон
dTub
Скачать

ማርያም ሲባል ቅር የሚልህ ወንድሜ ኢየሱስ አፉን የፈታው ማርያም እያለ መሆኑን ላስታውስህ እወዳለሁ

Автор: ሰበን seben media

Загружено: 2025-12-05

Просмотров: 84

Описание:

ማርያም ሲባል ቅር የሚልህ ወንድሜ ኢየሱስ አፉን የፈታው ማርያም እያለ መሆኑን ላስታውስህ እወዳለሁ:: መቼም ለዚህም ጥቅስ እንደማትጠይቀኝ ተስፋ አደርጋለሁ::
ኢየሱስ ሲባል ቅር የሚልሽ እኅቴ ማርያም ከሰማይ ሰምታ ለልጅዋ ያወጣችው ስም ኢየሱስ እንደሆነ ላስታውስህ እወዳለሁ::
በእርግጥ ድንግል ማርያም ኢየሱስ ብላ ብትሰይመውም ስሙን ግን ለመጥራት ግን አንድ ቃል አልበቃት ብሎ ተቸግራ ነበር::
ገና በሆድዋ ውስጥ እያለ ወደ እርሱ ስትጸልይ "ነፍሴ ጌታን ታከብረዋለች:: መንፈሴም በአምላኬና በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች" ስትል ሰማናት:: ልጅዋ ከሆድዋ ሳይወጣ ከልጅዋ ጋር ንግግር የጀመረች እናት እንዴት ያለች ናት? ወደ ሆድዋ ራስዋን ዘንበል አድርጋ "ጌታዬ አምላኬ መድኃኒቴ" እያለች የምትጣራ እናት አይታችሁ ታውቁ ይሆን? በሆድዋ ውስጥ ዙፋኑን ለዘረጋው ንጉሥ ጸሎት የምታሰማ እናት እንደምን ያለች ናት?
ከወለደችው በኋላስ ማን ብላ ጠርታው ይሆን? ገና ሕፃን ሳለ ምን ብላ አቅፋ አስተኛችው ይሆን? ምን ብላስ መገበችው?
የልደት መዝሙሩን "እሹሩሩ" (lullaby) ብሎ የሰየመው ቅዱስ ኤፍሬም ድንግል ማርያም ልጅዋን ምን እያለች ታስተኛው ይሆን? ብሎ በእርስዋ ቦታ ይጨነቃል:: በእርስዋ አንደበት ሆኖ እንዲህ ሲል ወደ ልጅዋ ይዘምራል::
" አንተ ምንጭ ሆይ ለአንተ ለማጠጣት የጡቶችን
ምንጭ እንዴት ልከፍታቸው ይቻለኛል? ሁሉን
ከገበታህ የምትመግብ ሆይ እኔ አንተን ልመግብህ
እንዴት ይቻለኛል? የክብርን ነጸብራቅ የተጎናፀፍከው
ሆይ እንደምን በጨርቅ ልጠቀልልህ እችላለሁ?"
ለአንተ እንዴት ያለ የማባበል ዜማን ላዜምልህ
እችላለሁ? እንደማንኛውም ሕፃን ለአንተ እሹሩሩ ብዬ
እንዳልዘምርልህ እንደ ማንኛውም ሰው ተራ ልደትን
የተወለድህ አይደለህም፡፡ ፅንሰትህ አዲስ ነው ፤
ልደትህም ተአምር ነው፡፡ በመንፈስ ካልሆነ ለአንተ
ሊዘምር የሚችል ማን ነው?’
ድንግል ማርያም ሆድዋ ውስጥ ሳለ አምላኬ መድኃኒቴ ያለችው ልጅዋን ካደገ በኋላ ምን ብላ ጠርታው ይሆን ብዬ በዐሥራ ሁለት ዓመቱ በቤተ መቅደስ እስክታገኘው ጠብቄ ተከትያት ገባሁ:: ከአይሁድ መምህራን ሥር ቁጭ ብሎ በንግግሩ ያስደንቃቸዋል:: (ሉቃ. 2:48)
ምን ብላ ትጠራው ይሆን ብዬ አንደበትዋን ስጠባበቅ
"ልጄ ሆይ" አለችው:: እኛ አባታችን ሆይ የምንለውን ፈጣሪ ልጄ ሆይ አለችው::
ድንግል ማርያም ለልጅዋ የሚበቃው ስም አጥታለት ነበርና እርሱን የምትጠራበት ብዙ ስም ነበራት:: በእናቶቻችን "ማን ብዬ ልጥራው ስምህን" ዜማ ድንግሊቱ ተጨንቃለች::
"ማን ብዬ ብጠራህ ይሻለኛል? ልጄ ብዬ ልጥራህ? ወንድሜ ልበልህ? ሙሽራዬስ ብዬ ልጥራህ? ጌታዬስ ልበልህ? ከዳዊት ቤት እንደመሆኔ እኅትህ ነኝ፡፡ ስለፀነስሁህ እናትህ ነኝ ፤ ስለ ንጽሕናህ ሙሽራህ ነኝ ፤ መድኃኒቴ ነህና ባሪያህና ልጅህ ነኝ’
አምላኬ ጌታዬ መድኃኒቴ ልጄ!
(St. Ephrem The Syrian, Harp of Spirit)
ማርያምና ኢየሱስ የሚሉት ስሞች ወንጌላውያን ሁለት ጎራ ይዘው የተጣሉባቸው ሳይሆኑ በምናከብረው ወንጌል ላይ አብረው የተጻፉ ስሞች ናቸው::ኢየሱስ የሚለው ስም ከድንግል ማርያም አፍ በፍቅር የሚፈስስ ጥዑም ስም ነበረ:: ማርያም የሚለው ስም ደግሞ ኢየሱስ ከሰው ልጆች ሁሉ በላይ በእናት ፍቅር ሆኖ የጠራው ጥዑም ስም ነው::
የልጅዋ ስም ሲጠራ የምታዝን ማርያም የእናቱ ስም ሲጠራ የሚናደድ ኢየሱስም የለም::
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ኅዳር ጽዮን 2018 ዓ.ም.

ማርያም ሲባል ቅር የሚልህ ወንድሜ ኢየሱስ አፉን የፈታው ማርያም እያለ መሆኑን ላስታውስህ እወዳለሁ

Поделиться в:

Доступные форматы для скачивания:

Скачать видео mp4

  • Информация по загрузке:

Скачать аудио mp3

Похожие видео

ነይ ነይ እምዬ ማርያም || ገብርኤል በሰማይ || በዘባነ ኪሩብ || ዘማሪ ዲያቆን ፍሬዘር ደሳለኝ@21media27

ነይ ነይ እምዬ ማርያም || ገብርኤል በሰማይ || በዘባነ ኪሩብ || ዘማሪ ዲያቆን ፍሬዘር ደሳለኝ@21media27

እቴ ሙሽራዬ || ግቢ  ገብርኤል | ዘማሪ ዲያቆን ፍሬዘር ደሳለኝ @21media27

እቴ ሙሽራዬ || ግቢ ገብርኤል | ዘማሪ ዲያቆን ፍሬዘር ደሳለኝ @21media27

ሰላም ለኪ || ልዩ ዝማሬ በሚሊኒየም አዳራሽ || በዘማሪ ዲያቆን ፍሬዘር ደሳለኝ  @21media27

ሰላም ለኪ || ልዩ ዝማሬ በሚሊኒየም አዳራሽ || በዘማሪ ዲያቆን ፍሬዘር ደሳለኝ @21media27

Eritrean Orthodox Tewahdo Mezmur|| ናይ ኣዴና ቅድስት ድንግል ማርያም መዛሙር ቅድስት ተዋህዶ!

Eritrean Orthodox Tewahdo Mezmur|| ናይ ኣዴና ቅድስት ድንግል ማርያም መዛሙር ቅድስት ተዋህዶ!

Prawda o witaminie D wyszła na jaw...

Prawda o witaminie D wyszła na jaw...

ШОКИРУЮЩЕЕ интервью пленного «МОНАХА». Из МОНАСТЫРЯ на ФРОНТ: «Я искал ТАМ СМЕРТЬ» | «Хочу жить»

ШОКИРУЮЩЕЕ интервью пленного «МОНАХА». Из МОНАСТЫРЯ на ФРОНТ: «Я искал ТАМ СМЕРТЬ» | «Хочу жить»

ማኅደረ መለኮት ። Mahdere Melekot ብህጻናት መዘምራን ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን Eritrean Orthodox Tewahdo ሕዳር ጽዮን

ማኅደረ መለኮት ። Mahdere Melekot ብህጻናት መዘምራን ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን Eritrean Orthodox Tewahdo ሕዳር ጽዮን

የሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል አከባበር በ ጉራጌ ሐገረ ስብከት ከሚገኘው ከ አበኬ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን

የሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል አከባበር በ ጉራጌ ሐገረ ስብከት ከሚገኘው ከ አበኬ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን

Dengel Fetariwan Weledechiw

Dengel Fetariwan Weledechiw

ПРЯМО СЕЙЧАС: Пророчество Мессинга о 18 декабря ВЫПОЛНЯЕТСЯ

ПРЯМО СЕЙЧАС: Пророчество Мессинга о 18 декабря ВЫПОЛНЯЕТСЯ

ХАЧАПУРИ!!! ЗА 10 МИНУТ! НА КЕФИРЕ! Съедаются в один миг!

ХАЧАПУРИ!!! ЗА 10 МИНУТ! НА КЕФИРЕ! Съедаются в один миг!

Wudase Mariam

Wudase Mariam

ለክብርሽ - LEKIBERESH ዘማሪ እዝራ ኃ/ሚካኤል @EziraHailemichel Live performance Orthodox

ለክብርሽ - LEKIBERESH ዘማሪ እዝራ ኃ/ሚካኤል @EziraHailemichel Live performance Orthodox

ለማርያም ድንግል መንበረ ተድላ//new vcd zimare by Zemarit Azeb Kebede

ለማርያም ድንግል መንበረ ተድላ//new vcd zimare by Zemarit Azeb Kebede

Эти 9 Ловушек преподносят под видом Доброты - Это должен знать каждый! Еврейская мудрость

Эти 9 Ловушек преподносят под видом Доброты - Это должен знать каждый! Еврейская мудрость

Przestań jeść takie JAJKA – robisz sobie krzywdę!

Przestań jeść takie JAJKA – robisz sobie krzywdę!

🔴አዲስ ቪዲዮ

🔴አዲስ ቪዲዮ "ናና አማኑኤል"ዘማሪት ሲስተር ሕይወት ተፈሪ nana amanuel video @zemarithiwotOfficial

Eritrean Orthodox Tewhado Mezmur Ade Alatni ~ ኣደ ኣላትኒ

Eritrean Orthodox Tewhado Mezmur Ade Alatni ~ ኣደ ኣላትኒ

Ходорковский раскрыл реальный финал войны: дальше начнётся самое опасное

Ходорковский раскрыл реальный финал войны: дальше начнётся самое опасное

⚡️ Зеленский пошёл на условия || Сделка с Путиным | Переговоры в Берлине

⚡️ Зеленский пошёл на условия || Сделка с Путиным | Переговоры в Берлине

© 2025 dtub. Все права защищены.

  • Контакты
  • О нас
  • Политика конфиденциальности

Контакты для правообладателей: [email protected]