Популярное

Музыка Кино и Анимация Автомобили Животные Спорт Путешествия Игры Юмор

Интересные видео

2025 Сериалы Трейлеры Новости Как сделать Видеоуроки Diy своими руками

Топ запросов

смотреть а4 schoolboy runaway турецкий сериал смотреть мультфильмы эдисон
dTub
Скачать

የጥቅምት 23 ሥንክሳር

Автор: kesisephrem

Загружено: 2025-11-01

Просмотров: 128

Описание:

ስንክሳር ዘወርኀ ጥቅምት 23

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ጥቅምት ሃያ ሦስት በዚች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ኀምሳ ሁለተኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሴፍ አረፈ ። ይህም አባት ከመኑፍ አገር ከታላላቆች ተወላጆች ወገን ነው ወላጆቹም ብዙ ገንዘብ ያላቸው ነበሩ ታናሽም ሁኖ ሳለ አባትና እናቱ ትተውት ሲሞቱ ድኃ አደግ ሆነ አንድ እግዚአብሔርንም የሚወድ ሰው አሳደገው ።

አድጎ በጎለመሰም ጊዜ የወላጆቹን ገንዘብ ሁሉንም ወስዶ ለድኆችና ለምስኪኖች መጸወተ ከዚህም በኋላ ወደ አስቄጥስ ገዳም ወጥቶ ከአንድ ፃድቅ ሽማግሌ ሰው አባት ዘንድ መነኰሰ በበጎ ገድል ሁሉ እየተጋደለ ኖረ ።

ዳግማዊ አባ ማርቆስም ሊቀ ጵጵስና በተሾመ ጊዜ የዚህን አባ ዮሴፍን በጎ ጠባዩንና የትሩፋቱን ዜና ሰምቶ መልእክተኞችን ልኮ ወደርሱ አስመጣው በቤቱም አኖረው ።

ከብዙ ወራትም በኋላ አባ ዮሴፍ ሊቀ ጳጳሳቱን አባ ማርቆስን ወደ አስቄጥስ ገዳም እሔድ ዘንድ ተወኝ ብሎ ለመነው ያን ጊዜም ቅስና ሹሞ አሰናበተው ሊቀ ጳጳሳት አባ ስምዖንም እስከ አረፈ ድረስ በዚያ በእስቄጥስ ገዳም ኖረ ከዚህም በኋላ የግብጽ አገር ያለ ሊቀ ጳጳሳት ብዙ ወራት ኖረች ።

ከዚህም በኋላ ኤጲስቆጶሳቱ መማለጃ ስለተቀበሉ ከአንድ ሚስቱ ከሞተችበትና መዓስብ ከሆነ ጸሐፊ ጋር ሊቀ ጵጵስና ይሾሙት ዘንድ ተስማሙ እኩሌቶቹ ግን ተቃወሟቸው እንዲህም አሏቸው የአባቶቻችን ቀኖና መማለጃ የሚቀበለውን ሁሉ ወይም ስለ ክህነት ሹመት መማለጃ የሚሰጠውን ያወግዛል ። ይልቁንም ይህ ሰው ሚስት አግብቷል እንዴት ሊሾም ይችላል በወንጌላዊ ማርቆስ ወንበር ላይ የሚሾም ንጹሕ ድንግልም ነውና ።

ይህንንም በአሏቸው ጊዜ ፈሩ ተመልሰውም ተስማሙ ለዚች ለከበረች ሹመት የሚሻለውን ይገልጽላቸው ዘንድ ክብር ይግባውና ወደ ጌታችን በአንድ ምክር ሁነው ጸለዩ እግዚአብሔርም ሰምቷቸው ለዚች የከበረች ሹመት የሚሻል አባ ዮሴፍ እንደሆነ አሳሰባቸው ።

ከዚህም በኋላ አባ ዮሴፍን ያመጡት ዘንድ ወደ አስቄጥስ ገዳም መልእክተኞችን ላኩ መልክተኞችም ይህን አባት ዮሴፍን የመረጥከው ከሆነ ምልክትን ትገልጥልን ዘንድ አቤቱ እንለምንሃለን የቤቱም ደጃፍ ክፍት ሁኖ ካገኘን ምልክት ይሁንልን ብለው ወደ እግዚአብሔርለመኑ ።

በደረሱም ጊዜ አንዱን መነኰስ እየሸኘ የበዓቱም ደጃፍ ክፍት ሁኖ አባ ዮሴፍን አገኙት በአያቸውም ጊዜ መንፈሳዊ ሰላምታ በመስጠት እጅ ነሣቸውና በደስታ ተቀብሎ ወደ በዓቱ አስገባቸው በዚያንም ጊዜ ለአባ ዮሴፍ ሊቀ ጵጵስና ይገባዋል ይገባዋል ይገባዋል እያሉ ይዘው አሠሩት ። እርሱ ግን እኔ ብዙ ኃጢአትን ሠርቻለሁና ይህ የከበረ ሹመት አይገባኝም እያለ ይጮህ ነበር እነርሱም ወደ እስክንድርያ ከተማ ወስደው ሊቀ ጵጵስና ሾሙት እንጂ ምንም ምክንያት አልተቀበሉትም ።

በወንጌላዊ ማርቆስ ወንበርም በተቀመጠ ጊዜ ለአብያተ ክርስቲያን እጅግ የሚያስብ ሆነ ለርሱ የሆነውን የግብሩን ገቢ ወስዶ ምድሮችን በመግዛት ለአብያተ ክርስተያን መተዳደሪያ ሊሆኑ ጉልቶች ያደርጋቸው ነበርና ።

አዘውትሮም ሕዝቡን የሚያስተምራቸው ሆነ በምንም በምን ለየአንዳንዱ ቸለል አይልም ነገር

ግን ሰይጣን ስለቀናበት ያለ ኀዘን አልተወውም ። ይህም እንዲህ ነው በምስር አገር የተሾሙ ሁለት ኤጲስቆጶሳት በሕዝቡ ላይ ክፉ ነገር በማድረግ በማይገባ ሥራ አስጨነቋቸው እርሱም በርኅራኄና በፍቅር መንጎቻቸውን እንዲጠብቁ አዘዛቸው ለመናቸውም እነርሱ ግን ሰምተው ከክፋታቸው አልተመለሱም ።

በሕዝቡም ላይ ችግርን በአበዙ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉም በጠቅላላ ወደ ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሴፍ መጡ በፊቱም እንዲህ ብለው ጮኹ እሊህን ኤጲስቆጶሳት ከላያችን ካላነሣሃቸው እኛ ወደሌላ ሃይማኖት እንገባለን አባ ዮሴፍም በመካከላቸው ሰላምን ለማድረግ ብዙ ትግልን ታገለ ግን አልተቻለውም ።

ከዚህም በኋላ በግብጽ አገር ያሉትን ኤጲስቆጶሳት ለጉባኤ ሰበሰባቸውና ስለ እሊህ ሁለት ኤጲስቆጶሳት ነገራቸው አሁንም ከመንጋዎቻቸው ጋር ሊአስታርቅ ሽቶ እሊህን ኤጲስቆጶሳት ወደ ጉባኤው አስቀረባቸው እነርሱ ግን የጉባኤውንም የእርሱንም ቃል አልተቀበሉም ስለዚህም ያ ጉባኤ ከሹመታቸው ሻራቸው ።

እነርሱም ወደ ግብጽ ንጉሥ ሒደው በሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሴፍ ላይ በሐሰት ነገር ሠሩበት ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሴፍንም ያመጡት ዘንድ ንጉሡ ወንድሙን ከጭፍራ ጋር ላከው ። የንጉሡም ወንድም ወደ ሊቀ ጳጳሳቱ በደረሰ ጊዜ ተበሳጨ ሊገለውም ወዶ ሰይፉን መዞ ሊቀ ጳጳሳቱን ሊመታው ሰነዘረበት ግን እጁ ወደ ሌላ አዘንብሎ ምሰሶ መትቶ ሰይፉ ተሰበረ እጅግም ተቆጥቶ ሌላ ሰይፍን መዝዞ በመላ ኃይሉ መታው ያን ጊዜም ሰይፉ ከአንገቱ ወደ ወገቡ ተመልሶ ልብሱንና ቅናቱን ብቻ ቆረጠ የንጉሡም ወንድም ከክፋት ንጹሕ እንደሆነ ስለዚህም አምላካዊት ኃይል እንደምትጠብቀው አሰበ አስተዋለም ።

ወደ ንጉሡም በክብር አደረሰው ወንድሙ ለሆነ ንጉሥም በእርሱ በሊቀ ጳጳሳቱ ላይ የሆነውን ሁሉ ነገረው ንጉሡም ፈራው አከበረውም ከዚህም በኋላ ስለከሰሱት ስለ ሁለቱ ኤጲስቆጶሳት ጠየቀው እርሱም ስለ ክፉ ሥራቸው በጉባኤ እንደተሻሩ እውነቱን ለንጉሡ አስረዳው ያን ጊዜም ሐሰተኞች እንደሆኑ ንጉሥ አወቀ ይገድሏቸውም ዘንድ አዘዘ ።

ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሴፍም ንጉሡን እንዲህ ብሎ ማለደው ጌታችን በክፉ ፈንታ በጎ እንድናደርግ እኛን አዞናልና ስለ እግዚአብሔር ብለህ እሊህን ማራቸው እንጂ አትግደላቸው ንጉሡም ስለ የዋህነቱ አደነቀ ልመናውንም ተቀብሎ ማረለት ።

ከዚህም በኋላ በሹማምንቱና በኤጲስቆጶሳቱ ሁሉ ላይ የፈለገውን ያደረግ ዘንድ ቢፈልግ እንዲሾም ወይም እንዲሽር የሚቃወመው እንዳይኖር ደብዳቤ በመጻፍ ሥልጣንን ሰጠው ።

በዚህም አባት ዘመን የኢትዮጵያ ንጉሥ ወደዚህ አባት ወደ ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሴፍ እንዲህ ብሎ መልእክትን ላከ ለወንጌላዊ ማርቆስ መንበርና በላዩ ለመቀመጥ ለተገባው ቅድስናህ እጅ እነሣለሁ በእኔና በመንግሥቴ ላይ በመላው ወገኖቼ በኢትዮጵያ ሰዎች ላይ ይቅርታ እንድታደርግና አባታችንን አባ ዮሐንስን እንድትልክልን እለምንሃለሁ ከሀገራችን ሰዎች ከእውነት መንገድ የወጡና የሳቱ ጳጳሳችንን አባ ዮሐንስን እኔ ሳልኖርና ሳላውቅ አባረውታልና ስለዚህም በሀገራችን ቸነፈርና ድርቅ ሁኖ ከሰዎችም ከእንስሶችም ብዙዎች አለቁ ።

አሁንም አባቴ ሆይ ስንፍናችንን ይቅር በል መሐሪና ይቅር ባይ ወደ ሆነ እግዚአብሔር ፈጽሞ ይማልድልን ዘንድ በከበረች ጸሎቱም ከዚህ መከራ እንድን ዘንድ አባታችንን አባ ዮሐንስን ላክልን ።

አባቴ ሆይ የተባረረበትን ምክንያት እኔ አስረዳሃለሁ እኔ ልጅህ ከአባቴ ከጳጳስ አባ ዮሐንስ ቡራኬ ተቀብዬ እርሱ ከሠራዊቴ ጋር በፍቅር አሰናብቶኝ ወደ ጦር ሜዳ ሔድሁ ከጦርሜዳም በተመለስኩ ጊዜ አባቴን አባ ዮሐንስ ጳጳሱን አጣሁት ስለርሱም በጠየቅሁ ጊዜ በቀድሞ ዘመን ዮሐንስ አፈ ወርቅን ንግሥት አውዶክስያ እንዳሳደደችው በክፉዎች ሰዎች ምክር ንግሥቲቱ ሚስቴ ማሳደዷን የቀኖናውንም ትእዛዝ በመተላለፍ በፈቃዳቸው ሌላ ጳጳስ እንየሸሙ ነገሩኝ ::

እንደሾሙ ነገሩኝ ።
እርሱ አባ ዮሐንስም ከኢትዮጵያ በአሳደዱት ጊዜ ወደ አስቄጥስ በመሔድ አስቀድሞ በመነኰሰባት በአባ ሙሴ ጸሊም ገዳም በዚያ ተቀመጠ ። የኢትዮጵያ ንጉሥ መልእክትም ወደ ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሴፍ በደረሰች ጊዜ አነበባት ስለ ኢትዮጵያ ንጉሥ የሃይማኖት ጽናት እጅግ ደስ አለው ፈጥኖም ወደ አስቄጥስ ገዳም መልእክተኞችን ልኮ አባ ዮሐንስን ወደርሱ አስመጥቶ አረጋጋው አጽናናው ከዚያም በኋላ ከደጋጎች ሰዎች ጋር ወደ ኢትዮጵያ አገርላከው ።

አባ ዮሐንስም ወደ ኢትዮጵያ አገር በደረሰ ጊዜ ቸነፈር ተወገደ ዝናብም ዘነበ ንጉሡና መላው የኢትዮጵያ ሰዎች ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑት ። ይህም ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሴፍ መናፍቃንን የሚገሥጻቸው ሆነ ሕዝቡንም ከአባቶቻቸው በተቀበሏት በቀናች ሃይማኖት እንዲጸኑ አስተማራቸው ከቅዱሳት መጻሕፍትም ለእነርሱም ሥውር የሆነውን ተርጉሞ ያስረዳቸዋል ያስገነዝባቸዋልም በትምህርቱና በጸሎቱም እንዲህ ጠበቃቸው ጌታችንም በእጆቹ ብዙዎች ተአምራትን አደረገ ያማረች ገድሉንም ፈጽሞ እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም በፍቅር አረፈ ። መላ የሕይወቱም ዘመን ሰባ ስምንት ነው ከምንኲስና በፊት ሃያ አመት በምንኲስና ተጋድሎ ሠላሳ ዘጠኝ ዓመት በሊቀ ጵጵስና ሹመት ዓሥራ ዘጠኝ ዓመት ኖረ ።

ለእግዚአብርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑርለዘላለሙ አሜን ።



በዚችም ቀን የቆሮንቶስ አገር ኤጲስቆጶስ ዲዮናስዮስ በዐላውያን ነገሥታት በዲዮቅልጥያኖስና በመክስምያኖስ ዘመን በሰማዕትነት አረፈ ይህንንም ቅዱስ በያዙት ጊዜ ብዙ ሥቃይን አሠቃዩት ማሠቃየቱንም በሰልቹ ጊዜ ራሱን በሰይፍ አስቆረጡት የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበለ በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን ።

በዚችም ቀን የቅዱሳን ኢላርዮስ፣ ጣንቅያቅ፣ ቴዎዶስዮስ፣ ቴዎላስ፣ ዮሳብና ገድላ፣ የሰማዕት እስክንድርያም መታሰቢያቸው ነው ። በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን ።
@መንፈሣዊ@ኦርቶዶክሳዊ‪@ሕይወት‬

የጥቅምት 23 ሥንክሳር

Поделиться в:

Доступные форматы для скачивания:

Скачать видео mp4

  • Информация по загрузке:

Скачать аудио mp3

Похожие видео

Bedenkuane

Bedenkuane

Мел Гибсон Всё Раскрывает | Это Действительно Произошло В Страстях Христовых | Х.Х. Бенитес

Мел Гибсон Всё Раскрывает | Это Действительно Произошло В Страстях Христовых | Х.Х. Бенитес

የነፍሴ ጥያቄ |  ኦርቶዶክስ ማለት ምን ማለት ነው? |  ሊቀ ሊቃውንት ስምዐኮነ መልአክ | ክፍል 1

የነፍሴ ጥያቄ | ኦርቶዶክስ ማለት ምን ማለት ነው? | ሊቀ ሊቃውንት ስምዐኮነ መልአክ | ክፍል 1

ልዩ አዲስ መዝሙር

ልዩ አዲስ መዝሙር "ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሀገር ናት" ዘማሪት ሰብለወንጌል እሸቴ @-mahtot

Ethiopia:- የኪዳነ ምህረት ተወዳጅ መዝሙሮች ስብስብ || Kidanemihret Mezmur Collection

Ethiopia:- የኪዳነ ምህረት ተወዳጅ መዝሙሮች ስብስብ || Kidanemihret Mezmur Collection

የጥቅምት 22 ሥንክሳር #ቅዱስ ሉቃስ #የቆረጠ እጅ እንዴት ይቀጠላል#የቅዱስ ዑራኤል ድርሳን#ባሮክ ያየው ራዕይ

የጥቅምት 22 ሥንክሳር #ቅዱስ ሉቃስ #የቆረጠ እጅ እንዴት ይቀጠላል#የቅዱስ ዑራኤል ድርሳን#ባሮክ ያየው ራዕይ

Успокаивает, восстанавливает нервную систему 🌿 Перестаньте думать, музыка для снятия стресса #4

Успокаивает, восстанавливает нервную систему 🌿 Перестаньте думать, музыка для снятия стресса #4

"ያወረድከው መና" በስብሐተ ነግህ ሰ/ት/ቤት መዘምራን ህዳር ፳፻፲፰ ዓ.ም || @snegih

"እጅ ቆረጠ የተባለው ሰው ከቀናት በፊት ለብልጽግና እጅ ሰጥቷል" | አርበኛ አበበ ፈንታው

ОСЕННЕЕ ОЧАРОВАНИЕ🌺Эту песню о любви слушают все🌿Великолепная музыка Сергея Грищука

ОСЕННЕЕ ОЧАРОВАНИЕ🌺Эту песню о любви слушают все🌿Великолепная музыка Сергея Грищука

Расслабляющая музыка, исцеляющая от стресса, беспокойства и депрессивных состояний, исцеляет #19

Расслабляющая музыка, исцеляющая от стресса, беспокойства и депрессивных состояний, исцеляет #19

WIELBŁĄD NEUERA, GOL WONDERKIDA, POPIS KANONIERÓW! ARSENAL - BAYERN, SKRÓT MECZU

WIELBŁĄD NEUERA, GOL WONDERKIDA, POPIS KANONIERÓW! ARSENAL - BAYERN, SKRÓT MECZU

የሕዳር 16ሥንክሳር#ለኪዳነ ምህረት ወዳጅ ብቻ#ፍቅርተ ክርሰቶስ #እመምዑዝ #የካዎች#ኦርቶዶክሳውያን#እንጦጦ

የሕዳር 16ሥንክሳር#ለኪዳነ ምህረት ወዳጅ ብቻ#ፍቅርተ ክርሰቶስ #እመምዑዝ #የካዎች#ኦርቶዶክሳውያን#እንጦጦ

ተወዳጅ  የሆኑ የቅዱስ ሚካኤል መዝሙሮች ስብስብ || ye kidus michael mezmur collection orthodox

ተወዳጅ የሆኑ የቅዱስ ሚካኤል መዝሙሮች ስብስብ || ye kidus michael mezmur collection orthodox

የጥቅምት 29 ሥንክሳር#ልደተ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ #ቅድስት  ፍቅርተ ክርስቶስ#ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ

የጥቅምት 29 ሥንክሳር#ልደተ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ #ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ#ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ

Самая красивая мелодия в мире🌿Осень! НЕВЕРОЯТНО КРАСИВЫЕ И ЛУЧШИЕ ПЕСНИ ДЛЯ ДУШИ🌿Сергей Грищук

Самая красивая мелодия в мире🌿Осень! НЕВЕРОЯТНО КРАСИВЫЕ И ЛУЧШИЕ ПЕСНИ ДЛЯ ДУШИ🌿Сергей Грищук

Eska Hity Listopad 2025 🎶 Najgorętsze Hity 2025 – Polska Viral Playlist Vol.26

Eska Hity Listopad 2025 🎶 Najgorętsze Hity 2025 – Polska Viral Playlist Vol.26

Tewahdo Haymanote

Tewahdo Haymanote

ПЕСНИ ВЕЧНОСТИ – Альбом из 1️⃣0️⃣ песен – Maranata Brothers

ПЕСНИ ВЕЧНОСТИ – Альбом из 1️⃣0️⃣ песен – Maranata Brothers

Eska Hity Listopad 2025 🎵 Najlepsza Muzyka Radia – Gorące Polska Hit Mix Vol.03

Eska Hity Listopad 2025 🎵 Najlepsza Muzyka Radia – Gorące Polska Hit Mix Vol.03

© 2025 dtub. Все права защищены.



  • Контакты
  • О нас
  • Политика конфиденциальности



Контакты для правообладателей: [email protected]