የሕዳር 17ሥንክሳር
Автор: kesisephrem
Загружено: 2025-11-25
Просмотров: 87
ስንክሳር ዘወርኀ ኅዳር 17
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ኅዳርዐሥራ ሰባት በዚች ቀን ታላቅና ክቡር የሆነ የዓለሙ ሁሉ መምህርየቊስጥንጥንያ ሊቀ ጳጳሳት የዮሐንስ አፈወርቅ ሥጋው የፈለሰበት ነው
ይህም እንዲህ ነው መበለቲቱን ቦታዋን በግፍ ነጥቃታለችና እርሱም እንድትመልስላት ቢያዛት ስለ አልሰማችው ስለ መበለቲቱ ቦታ ቅዱስ ዮሐንስ ንግሥት አውዶክስያን በአወገዛት ጊዜ በእርሱ ላይ ተቆጣች ሰይጣንም በልቧ አደረና ስለ ክፉ ሥራቸውና ስለ በደላቸው አውግዞ የለያቸውን ኤጲስቆጶሳት በእርሱ ላይ ሰበሰበች ። እነርሱም ስለ መሰደዱ ከእርሷ ጋር ተስማምተው አድራኮስ ወደምትባል ደሴት አጋዘችው በዚያም ጥቂት ዓመታት ኑሮ ወደ መንበረ ሲመቱ ተመለሰ ።
ከዚህም በኋላ ዳግመኛ መናፍቃን የሆኑ ኤጲስቆጶሳትን ሰበሰበችና ወደ አርማንያ አጋዙት ከዚያም በረሀ ወደ ሆነ ሩቅ አገር ሰደዱትና በዚያ አረፈ ።
የአርቃዴዎስም ልጅ ታናሹ ቴዎዶስዮስ በነገሠ ጊዜ መልክተኞችን ልኮ የቅዱስ ዮሐንስን ሥጋ ብዙ በመዘመርና በማመስገን በታላቅ ክብር ወደ ቊስጥንጥንያ አፍልሶ አስመጣው ይህም ከዕረፍቱ በኋላ በሠላሳ አምስት ዓመት ነው ። በሌላ በቅብጢ መጽሐፍ በግንቦት ወር ሃያ ሁለት ቀን እንደ ደረሰ ይናገራል በሮማውያን መጽሐፍ ግን በየካቲት ወር ሃያ ሁለት ቀን ተባለ የዕንቊ ፈርጾች ባሉት የዕብነ በረድ ሣጥን ውስጥ አድርገው ወደ ቤተ መቅደስ አስገቡት ከሥጋውም ታላላቅ የሆኑ ድንቆች ተአምራት ተገለጡ ።
ሁለተኛም የእስክንድርያ ግጻዌና የሀገረ ቅፍጥ ኤጲስቆጶስ አባ ዮሐንስ የጻፈው ግጻዌ የመለካውያንም ግጻዌ በዚች በኅዳር ዐሥራ ሰባት ቀን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳረፈባት ተባበሩ ። ሁለተኛም ደግሞ የመለካውያን ግጻዌ ዮሐንስ አፈወርቅ ዐይሉል በሚባል ወር በዐሥራ አራት እንዳረፈ ይናገራል ይህም በመድኃኒታችን በመስቀሉ በዓል መስከረም ዐሥራ ሰባት ቀን ነው ። ስለዚህም ራሱን ለማስቻል ወደ ኅዳር ዐሥራ ሰባት ቀን ለወጡት ። የቀደሙ መጻሕፍት ግን ዕረፍቱ ግንቦት ዐሥራ ሁለት ቀን እንደሆነ ያወሳሉ ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ በከበረ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን ።
በዚችም ዕለት የቡሩክ አብርሃምና የሚስቱ የሐሪክ መታሰቢያቸው ነው ዳግመኛም የወጺፍ ጻድቃን መታሰቢያቸው ሆነ ። በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን ።
በዚችም ዕለት ዳግመኛ ለማስተማር የተጠራ የአበ ምኔቱ የአባ ሲኖዳ መታሰቢያው ነው ። በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን ።
ኅዳር ፲፯ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ፍልሠቱ
፪.ቅድስት ወለተ ዼጥሮስ ኢትዮዽያዊት
፫.አባ ሲኖዳ ዘደብረ ጽሙና - ጐጃም
፬.ጻድቃን እለ ወጺፍ
፭.ቅዱሳን አብርሃምና ሐሪክ
፮.ቅድስት ወለተ ጳውሎስና ወለተ ክርስቶስ
ወርኀዊ በዓላት
፩.እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት
፪.ያዕቆብ ሐዋርያ
፫.መክሲሞስና ዱማቴዎስ
፬.አባ ገሪማ
፭.አባ ዸላሞን
፮.አባ ለትጹን
፯.ቅዱስ ኤዺፋንዮስ
በድካምና በጥረት: ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት: በራብና በጥም: ብዙ
ጊዜም በመጦም: በብርድና በራቁትነት ነበርሁ . የቀረውን ነገርሳልቆጥር ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው ። ፪ኛ ቆሮ. ፲፩፥፳፫
@እናታችንማርያምሆይእንወድ @kesishenokweldemariam2240 @EfoyZeOrthodox
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: