ታጣቂዎች ወደ ምክክር የመግባት ፍላጎት ካላቸው ከለላ እንዲሰጣቸው....
Автор: Sheger FM 102.1 Radio
Загружено: 2025-12-03
Просмотров: 433
ህዳር 24 2018
ታጣቂዎች ወደ ምክክር የመግባት ፍላጎት ካላቸው ከለላ እንዲሰጣቸው ከአለም አቀፉ ቀይ መስቀል እና ቀይ ጨረቃ ማህበር ጋር ውይይት ማድረጉን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተናገረ፡፡
ኮሚሽኑ ይህን የተናገረው ትናንት ህዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከሃይማኖት ተቋማት እና ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ጋር የተጀመረው ምክክር ውጤታማ እንዲሆን በመከረበት ወቅት ነው፡፡
ዶ/ር ሰይፈ የተባሉ የወይይቱ ተሳታፊ በምክክሩ ላይ እስካሁን ያልተሳተፉ አካላት ለምን መሳተፍ እንዳልፈለጉ ማብራሪያ ጠይቀው በትጥቅ ትግል ላይ ላሉ ታጣቂዎች ጥሪ ማድረግ ብቻውን በቂ ነው ወይ? ዋስትና አያስፈልግም ወይ? ዋስትና እንዲሰጣቸው አለም አቀፉን ማህበረሰብ ጠይቃቹሀዋል ወይ? ሲሉ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡
ለጥያቄው ምላሽ የሰጡት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር መሀሙድ ድሪር የታጠቁ አካላት በባህርያቸው በምክክር ወዲያው እንደማይሳተፉ ጠቁመው ምክንያቱ ደግሞ የመተማመን ጉድለቶች በመኖራቸው ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡
ታጣቂዎች መንግስትንም አያምኑም ‹‹መንግስት ነው የፈጠራቸው ብለው የሚያምኑትንም እኛንም አያምኑም›› ይህም በሁሉ ሀገር የታየ ጉዳይ ነው ሲሉ ኮሚሽነር ማሃሙድ ተናግረዋል፡፡
ይህን የመተማማን ችግር ለመፍታት ደግሞ የሃይማኖት አባቶች እና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ድርሻቸው ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡
ኮሚሽኑ ወደ ጓቲማላ፣ ኮሎምቢያ እና አየርላንድ ትምህርት ለመውሰድ ሄዶ እንደነበር ያስታወሱት ኮሚሽነሩ እነዚህ ሀገራት የታጠቁ አካላትን እንዴት ነው በምክክሩ ያሳተፏቸው የሚለውን ከመሪዎች እና ከሂደቱ ተሳታፊዎች ጋር ተወያይተናል ሲሉ አስረድተዋል፡፡
በመቀጠልም ኮሚሽኑ ወደ ጄኔቫ በማቅናት ከአለም አቀፉ ቀይ መስቀል እና ቀይ ጨረቃ ድርጅት ጋር ተነጋግሯል ብለዋል፡፡
እነሱን ያነጋገርነው ደግሞ ድርጅቶቹ ከእኛ የበለጠ በመተማመን ድልድይ ሆነው ሊያገለግሉ ይችላሉ በሚል ነው ሲሉ ኮሚሽነር ማሃሙድ ተናግረዋል፡፡
በዚህም ታጣቂዎች በፈለጉት ሰዓት ያለምንም ስጋት ወደ ምክክሩ የሚመጡበት መሰረት ተዘጋጅቷል ሲሉ ጠቁመዋል፡፡
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ታጣቂዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ታራሚዎች እና የትግራይ ክልል በምክክሩ መሳተፍ ለምክክሩ መሳካት ቁልፍ ጉዳይ ቢሆኑም እስካሁን እንዳልተሳተፉ እና ይህንም እንቅፋት እንደሆነበት አስረድቷል፡፡
ይህን በተመለከተ የትግራይ ክልል፣ ታጣቂዎች፣ ታራሚዎች እና የቀሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ካልተሳተፉ ኮሚሽኑ ምን ያደርጋል? የተጀመረው ምክክርስ በጅምር ይቀራል ወይ? የሚል ጥያቄም ከተሳታፊዎች ተነስቷል፡፡
የምክክር ኮሚሽን በበኩሉ በሰጠው ምላሽ እነዚህ አካላት በምክክሩ ካልተሳተፉ ምን ይደረግ በሚለው ላይ እስካሁን ከውሳኔ አልደረስኩም ብሏል፡፡
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ሙሉጌታ አጎ ለመሳተፍ ፍላጎት የሌላቸውን አካላት እንዴት እናድርግ የሚለውን ለመወሰን የሃይማኖት አባቶችን እና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን እገዛ እንፈልጋን ብለዋል፡፡
ታራሚዎችን በተመለከተ ግን በቀጣይ ሳምንታት አጀንዳዎችንን እንሰበስባለን ሲሉ አስረድተዋል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
👇👇👇
🌐Website፡ https://www.shegerfm.com/
🎥YouTube https://tinyurl.com/37tux478
🟦Telegram https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📘Facebook፡ https://tinyurl.com/4tx8t8wm
💬WhatsApp https://tinyurl.com/ycxjmm3s
🐦X : https://x.com/shegerfm?s=2
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: