መካከለኛችን ሐምሌት በልጁን Mekakelegnachin Hamlet Beljun 2025
Автор: Hamlet Beljun
Загружено: 2025-04-19
Просмотров: 7398
መካከለኛችን
ሰው ሰውን ቢበድል እግዚአብሔር ይፈርዳል፤
ቅዱስ ራሱ ተበድሎ ማን ያሸማግላል?
ማን ንጹሕ አለና የሚቀርብ ፊቱ?
በጽድቅ ጸንቶ ‘ሚቆም ሳይከስሰው ስሕተቱ!
ክብር ጎድሎታል ሁሉ ኀጢአትን ሠርቶ፣
የዐመፅ መንገዱ ሞትን አፍርቶ፤
እርቆ ሳለ ከሕይወት ወዲያ ማዶ
በልጁ ሞት ጠራው የአዳም ዘርን ወዶ።
የዓለምን ኀጢአት የሚያስወግደው፣
የመሥዋዕቱ በግ አብ ያዘጋጀው፣
የጠፋን ፍለጋ ወልድ ሆኖ ሥጋ፣
አብ ታረቀ ዓለሙን በመስቀሉ ዋጋ።
በምሕረቱ ባለጸጋ፣
በምሕረቱ ባለጠጋ፣
የደካሞች ወዳጅ ወደኛ ተጠጋ፤
የኢየሱስ ደም ከኀጢአት ያነጻል፤
ያመነ በስሙ ከአብ ቁጣ ተርፏል።
አዎ
በአፉ ተንኮል የለም፤ ይህ የእግዚአብሔር በግ፣ ኀጢአት የማያውቀው፣ ስህተት ‘ማያደርግ፣
በላዩ ወረደ ተግሳፅ የደኅንነት፣
አብ ቀድሞ እንዳሰበው ነቢያት እንዳወሩት። ሊያወጣን ወረደ ሊያድን ማለደ፣
ከሞት በበረታ ፍቅር ስለወደደን።
አስታራቂያችን መካከለኛችን (*2)
ኢየሱስ
በቁስልህ ዳነ ሕመማችን፤
በደምህም ዘላለማችን፤
የሀጥን በደል ተሸክመህ ፣
ዋጀኸን ነፍስህን ቤዛ ሰተህ።
ሊቀ ካህናት የምትማልድልን፤
ምትክ ሆይ፤ በአብ ፊት ታየህልን፤
ስንለብስ አንተ የክብር ልብስን፣
ለዘላለም ሕያው አደረግኸን።
ሞት መውጊያህ የታለ? ሲኦል ድል መንሣትህ?
አሸነፈ ኢየሱስ ሆነ ለኀጥእ ስርየት፣
ግድግዳው ፈረሰ በደል የገነባው፤
በሁለተኛው አዳም በቅዱሱ በግ ደም።
በምሕረቱ ባለጠጋ፣
የደካሞች ወዳጅ ወደ እኛ ተጠጋ፤
የኢየሱስ ደም ከኀጢአት ያነጻል፤
ያመነ በኢየሱስ ከመንፈስ ተወልዷል።
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: