የት ሄዳለው ጌታ Yet hedalehu Geta ዘማሪ አቤል ፍቅሬ Zemari Abel Fikre
Автор: Solen ሶለን
Загружено: 2024-11-09
Просмотров: 645
የት ሄዳለሁ ጌታ
የት ሄዳለሁ ጌታ የትሄዳለሁ
አምላኬ ከፊትህ የት ደርሳለሁ
እንደ ንስር ወደላይ ብመጥቅም
በዚያም አለህ እንጂ አላመልጥም
ብኮበልል ብሸሽም እንኳን ከፊትህ
መች ቀነሰ መቼስ ተለየ ምህረትህ
አወጣህኝ በቸርነትህ ከሸለቆ
ሰላሜ ነህ መኖር መልካም ነው አንተን አውቆ
ወሰን ገደብ የለውም ላንተ ድንበር
መረገጫ ናትና ለእግርህ ይች ምድር
ማንም ሸሽቶ ማምለጥ አይችልም ከፊትህ
ይህን አለም አበጃጅተዋል እጆችህ
ወደህኛል በማይሞት ፍቅርህ ለዘላለም
ካንተ ወዲያ በረከት ሰላም ከቶ የለም
አርፏል ዛሬ ተቅበዝባዥ ልጅህ ባንተ ጥላ
ስደት ይብቃኝ አልመለስም ወደ ኋላ
ጉም ጨለም ፍፁም አይችልም ሊጋርድህ
አልፈህኝ ነው አንተ ልጅህን በመውደድህ
ስንቴ ማርከኝ ስንቴስ አለፍከኝ በይቅርታ
ክበርልኝ መድኃኒቴ ሆይ የእኔ ጌታ
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: