Enbaye Ayiterahim | እንባዬ አይጠራህም | Selamawit Admassu New Gospel song
Автор: Selamawit Admassu official
Загружено: 2025-02-06
Просмотров: 1328
ይሄ ዝማሬ ከ13 አመታት በፊት በቁጥር አንድ የዝማሬ አለበሜ ላይ ከተካተቱት ዝማሬዎች አንዱ ነዉ።
💛ጸሎት 🙏
ይሄንን አፅናፈ አለም የፈጠረና የሚቆጣጠር፣ እጅጉን ታላቅ የሆነ አምላካችን ፤ከእኛ ከታናናሾች ጋር በየትኛውም የህይወት ጉዳዮቻችን እንድናነጋግረዉ ፣ በፍቅር የልባችንን እድናዋየዉ ፀሎት የሚባል ድልድይ ሰራልን። እንዴት ያለ ጥልቅ ሚስጥር ነዉ!!
ቅዱሳን ሆይ "በተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ታገሡ፤ በጸሎት ጽኑ፤” ተብሎ እንደተፃፈ ለፀሎት ትተጉ ዘንድ እያስታወስኩ ነገር ግን የምንፀልያቸዉ ፀሎቶቻችንን ቆም ብለን በቃሉ መፈተሽና እንደ ፈቃዱ መሆኑን ማረጋገጥ ያሻናል።
መዘንጋት የሌለብን ነገር በጌታ ዘንድ
በእዉነት እንጂ በእንባችን ብዛት ፀሎት አይመለስም ! ከአይኖቻችን በሚወርዱ የዉሃ ዘለላዎች ሀሳቡን የሚለዉጥ አምላክ የለንም።
እንደ ፈቃዱ ከሆነ ግን “አምናችሁም በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ ትቀበላላችሁ”ተብሎ እንደተፃፈ አምላክ ወደ ልመናችን ይመለከታል። ይመጣል። ይመልስልናልም።
ስለዚህ 👉 ከትናንት ይልቅ እንጸልይ፣ እንለምን፣ እንማልድ፣ እንማፀን፣ እንጠይቅ፣ ከምስጋና ጋር የልባችንን እናሳዉቅ። እንደፈቃዱ ይሁን እንጂ ጌታ ይሰማል🙏 በጊዜው ደግሞ ይመጣል !
💛💜💚
እንባዬ አይጠራህም አንተን እዉነትህ ከሌለ በልቤ
ቃሎቼ አይመቹህም ፈቃድህ ካልሆነ ፈቃዴ
ካልሆነ ፈቃዴ
እልፍኜ ልግባ በሬንም ልዝጋ
ለብቻችን ነን ላዉራልህ ጌታ
የዝምታዬ ቃል ይገባሀል
አይንህ አካሌን ይመረምራል
ይመረምራል
ባማሩ ቃሎቼ አንተን አላሳምን
እዉነቱ ይሄ ነዉ እንባ አያያራርህም
ዝለዚህ የልቤን ኑሮዬ ይንገረህ
ፀሎቴ በዉበት በሞገስ ይታይህ
ልቤ እንደ ዉሃ ቢፈስልኝ
አይኔ ቢያነባ ቢጎርፍልኝ
ግን በዚህ ብቻ አንተ አትመጣም
በእዉነት እንጂ በእንባዬ አትረካም
በእንባዬ አትረካም
#Enbaye Ayeterahem #ሰላማዊት አድማሱ
#gospelmusic #newmusic #protestantmezmur #protestant #prayer #ethiopia #church #spirituality #habesha #Christianity
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: