የኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ ከ900 በላይ ተማሪዎችን በተለያዩ የሙያ ዘርፎች አስመርቋል
Автор: Amhara Agriculture Bureau
Загружено: 2025-06-30
Просмотров: 559
ድምፅና ምስል ቅንብር ኤዲተር : ጌታቸው ታፈረ
የኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ ከ900 በላይ ተማሪዎችን በተለያዩ የሙያ ዘርፎች አስመርቋል
ኮምቦልቻ፣ ሰኔ 22፣ 2017 ዓ/ም ( ግብርና ቢሮ ) የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ከግብርና ሚኒስቴርና ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በደረጃ አራት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ተማሪዎች በዛሬው ዕለት በኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ የምረቃ ስነ ስርዓት ተካሂዷል።
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ በግብርና ሚኒስቴር የእርሻና ሆርቲ ካልቸር ዘርፍ የኤክስቴንሽን መሪ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ የኔነሽ ኤጉ፣ የደቡብ ወሎ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አሊ ይማም፣ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የኤክስቴሽን ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ቀኝአዝማች መስፍን፣ የደቡብ ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ ሀላፊ አቶ አህመድ ጋሎ እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በግብርና ሚኒስቴር የእርሻና ሆርቲካለቸር ዘርፍ የኤክስቴንሽን መሪ ስራ አስፈፃሚና የእለቱ የክብር እንግዳ ወ/ሮ የኔነሽ ኤጉ እንደገለፁት የልማት አረበኛ የሆናችሁ የቀበሌ ልማት ጣቢያ ባለሙያዎች ደከመኝ፣ሰለቸኝ ሳትሉ ለአርሶ አደሩ ህይወት መሻሻል የምታደርጉት ከፍተኛ ጥረት የሚደነቅ ነው ብለዋል። ጥያቄዎችችሁን ለመመለስ የተቻለንን ሁሉ ጥረት እንደርጋለን ያሉት ወ/ሮ የኔነሽ ኤጉ በቀጣይም የደረጃ 1፣ የደረጃ 2 እና የደረጃ 3 ባለሙያዎች እናስተምራለን ሲሉ ገልፀዋል።
የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የኤክስቴሽን ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ቀኝአዝማች መስፍን በበኩላቸው የፌዴራል ግብርና ሚኒስቴር ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመቀናጀት በክልላችን ካሉ የደረጃ 3 ባለሙያዎች ውስጥ 903 ባለሙያዎችን በ6 የትምህርት ዘርፎች ወደ ደረጃ 4 ስልጠናውን ሙሉ ወጭ በመሸፈን ለዚህ ውጤት እንድትበቁ ላደረጉልን ከፍተኛ ድጋፍ በአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ስም ላቅ ያለ ምስጋና አቀርባለሁ ብለዋል።
በቀጣይም የደረጃ 2 ፣ ከዲፕሎማ ወደ ዲግሪና ከተቻለም ከዛ በላይ ድጋፍና እገዛችሁ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እንጠይቃለን ያሉት አቶ ቀኝ አዝማች መስፍን ክልሉም በራሱ አቅም በተከታታይ የባለሙያዎችን የመማር፣ የማወቅና፣ የማደግ ፍላጎት ለማሳካት በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ ሲሉ ተናግረዋል።
ውድ ሰልጣኞች እንደልፋታችሁና አስተዋፆአችሁ ከዚህ በላይ የሚገባችሁ ቢሆንም፣ በበጋ በፅሃይ፣ በክረምት በዝናብና በጭቃ እንዲሁም በፀጥታ ችግርም ውስጥ ጭምር ህይወት አስይዛችሁ ለምትሰጡት አገልግሎት ይህ የሚያንስባችሁ እንጅ የሚበዛባችሁ ባይሆንም ከ4 አመታት በላይ ተቋርጦ የቆየው የትምህርት ዕድል የመጀመሪያው ዙር ሰልጣኝ በመሆናችሁ እድለኞች ናችሁና በድጋሚ እንኳንም ለዚህ ቀን በቃችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
የኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጅ ዲን አቶ በዛብህ ይመር ተማሪዎች በቂ እውቀትና ክህሎት እንዲጨብጡ የሚያስችል የንድፈ ሀሳብና የተግባር ትምህርት መሰጠቱን ገልፀዋል። በደረጃ አራት በስድስት የትምህርት ዘርፎች በሰብል ልማት፣ በመስኖ፣ በተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ፣ በእንስሳት እርባታ፣ በእንስሳት ጤና እና በህብረት ስራ ማህበር ስልጠናቸውን ሲከታተሉ ቆይተው በዛሬው እለት ተመርቀዋል ብለዋል። 99 በመቶ ተማሪዎች የብቃት ማረጋገጫ ፈተና ( COC ) ወስደው ማለፋቸውን ተናግረዋል።
የኮምቦልቻ ግብርና ኮሌጁ በዛሬው እለት 903 ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን 446 ተመራቂዎች ሴቶች ናቸው።
ዘጋቢ:- አንተነህ ሰውአገኝ
ድምፅና ምስል ቅንብር ኤዲተር : ጌታቸው ታፈረ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ
ድረ-ገጽ http://www.amhboard.gov.et/
ቴሌግራም https://t.me/AmharaBureauofAgriculter
ፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?...
ዩትዩብ / @amharaagriculturebureau6055
ቲክቶክ / amhara.agricultur
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: