01 Hamlet Beljun | AHADU AMLAK | አሐዱ አምላክ
Автор: Hamlet Beljun
Загружено: 2025-09-11
Просмотров: 38400
Click This Link 👉 / @hamletbeljun #SUBSCRIBE
TO OUR YOU TUBE CHANNEL TO GET NOTIFICATIIONS OF NEW POSTS
አሀዱ አምላክ track 1
ማንስ በአይንህ ፊት ገዝፎ ተልቆብህ
ማንን 'አንቱ' ብለህ ትጠራዋህ?
ተራሮች ሳይወለዱ አለማት ሳይዋቀሩ
ከዘላለም በፊት የነበርክ ህያው አሀዱ አምላክ
ያለ የሚኖር ማንነትህ
ሁሉ ንብረትህ ነው ግዛትህ
ፍጥረት በፊትህ ሚንቀጠቀጥ
እንኩዋን የሰው ልጅ ግዑዝ ሚቀልጥ
ብትመሰገን ስለሌለህ እንከን
ብትወደስ ነህና ንጉስ
ብናመልክህ ጠፍቶ ሚመስልህ
አልፋ ኦሜጋ መጠሪያ ስምህ
ቃልህ አይታጠፍ ያልከው አያልፍ
ተሳስተህ አታውቅም አትታረምም
ካለመኖር መቷል ሁሉን ይሁን ስትል
እንኩዋንስ አንተ ስራህ ከአዕምሮ ያልፋል
ለከዋክብቱ ሰጠህ መጠሪያ
ለቀን ጨለማ መሰማሪያ
ሁሉን ደግፈህ በስልጣን ቃል
አለማት ፀኑ በማስተዋልህ
አቻ ቢሆን እኩያ የለህም መንትያ
በሰማይ በምድር አልተገኘልህ ወደር
ብትመሰገን ስለሌለህ እንከን
ብትወደስ ነህና ንጉስ
ብናመልክህ ጠፍቶ ሚመስልህ
አልፋ ኦሜጋ መጠሪያ ስምህ
ፍጥረት ከበታች ሚያይህ ወደላይ
ባንተ ባምላኩ በተስፋ ያድራል
እስትንፋስህን ብትሰበስበው
ስጋ ለባሽ ሁሉ አፈር ነው
አህዛብ በገንቦ እንዳለች ጠብታ
በ አንተ ሚዛን የታዪ ለታ
በማንም ግንባር ልብህ አይሸበር
ጉልበት ይገዛል አንተ ክብር
አቻ ቢሆን እኩያ የለህም መንትያ
በሰማይ በምድር አልተገኘልህ ወደር
ብትመሰገን ስለሌለህ እንከን
ብትወደስ ነህና ንጉስ
ብናመልክህ ጠፍቶ ሚመስልህ
አልፋ ኦሜጋ መጠሪያ ስምህ
©Hamlet Beljun Copyright
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: