New song | ለዋለው ውለታ | ዘማሪ በናያስ ብርሃኑ | Benayas Birhanu | Apostolic Church of Ethiopia
Автор: Iso Yisehak Ab
Загружено: 2025-05-27
Просмотров: 11794
ዘማሪ በናያስ ብርሃኑ
ግጥም/Lyric
ለዋለው ውለታ ምስጋና ያንሰዋል
አዎ ምስጋና ያንሰዋል
እልል ብንልለት መች ይበዛበታል
ለታላቅነቱ እልልታ ያንሰዋል
አዎ እልልታ ያንሰዋል
አይበዛበትም ክብር ይገባዋል
ላቆመን በክብር በምስጋና
ወድዶን በፊቱ እንደገና
ምንሰዋለት የእኛ ምስጋና
አይበዛበት ቅዱስ ነውና
1. ምንም በሌለበት በምድረበዳ ቃሉን አስይዞ
አፅንቶ ያቆመን ሲበረታብን የበረሃው ጉዞ
ለታመኑበት የሚታመን ቃሉን ማይረሳ
ያደርሳል ካለበት ከዙፋኑ ላይ ክንዱ ሲነሳ
ለዋለው ውለታ. . .
2. በሕይወት መኖራችን ዛሬም በቤትህ አንድም ሳንጠፋ
በክንፎችህ ጉያ ሸሽገኸን ነው ሰጥተኸን ተስፋ
እንዲህ ያማረብን ዛሬም በቤትህ ፊት የቆምነው
በአንተ ነው ኢየሱስ ታሪካችንም ሁሉ ያማረው
ለዋለው ውለታ. . .
3. ዓመታት ዘመናት ሲቀያየሩ ሲለዋወጡ
መከራ ፈተና ሲፈራረቁ ሰላም ሲያሳጡ
ወዳጅ ዘመድ ሲርቅ የሚታመን አንድም ሲታጣ
አለሁ ልጄ ብሎ ግን አንድ ወዳጅ ኢየሱስ መጣ
ለዋለው ውለታ. . .
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: