Популярное

Музыка Кино и Анимация Автомобили Животные Спорт Путешествия Игры Юмор

Интересные видео

2025 Сериалы Трейлеры Новости Как сделать Видеоуроки Diy своими руками

Топ запросов

смотреть а4 schoolboy runaway турецкий сериал смотреть мультфильмы эдисон
dTub
Скачать

አላህን ፈለኩት ኢየሱስን አገኘሁት ምስክርነት ||ከእስልምና ወደ ክርስትና || Nabeel Qureshi Amharic

Автор: እውነት ያሳርፋል Ewnet Yasarfal

Загружено: 2024-06-11

Просмотров: 114113

Описание:

I found this video useful, so I translated it to the best of my ability. Use this link to find the first video I translated from. I apologize for the minor mistakes I make.‌‌
   • Seeking Allah, Finding Jesus: The Christia...  

መልካም ዜና

የምስራች፣ የምስራች፣ የምስራች! የምስራች ማለት መልካም ዜና ማለት ነው። የእግዚአብሔር ቃል ደጋግሞ የሚነግረን ይሄ መልካም ዜና ምንድነው? ዛሬ፣ በእግዚአብሔር ረዳትነት፣ በእግዚአብሔር ቃል ላይ ስለተጠቀሰው ስለዚህ መልካም ዜና እንነጋገራለን። ነገር ግን ስለ መልካሙ ዜና ከመነጋገራች በፊት ስለ መጥፎው ዜና ማስታወስ አለብን።

ምንድነው መጥፎው ዜና? በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ከፈጠረ በኋላ አዳምንና ሔዋንን በምድራዊዋ ገነት ውስጥ እንዳስቀመጣቸው ታስታውሳላችሁ። እግዚአብሄር እንዲያውቁት፣ እንዲወዱት፣ እንዲታዘዙት እና ለዘላለም እንዲያከብሩት ፈጥሯቸዋል። ይሁን እንጂ እግዚአብሔር እነሱን ለመፈተን አዳምን እንዲህ አለው፡-
“በገነት ካለው ከዛፉ ፍሬ ብሉ፥ ነገር ግን እንዳትሞቱ በገነት መካከል ካለው ከዛፉ ፍሬ አትብሉ አትንኩትም።”

መጥፎው ዜና አዳምና ሔዋን እባቡን ማለትም ከተከለከለው ዛፍ ፍሬ እንዲበሉ የፈተናቸውን ዲያብሎስን ማዳመጣቸው ነው። የአዳምና የሔዋን ኃጢአት እነርሱንና ዘሮቻቸውን ሁሉ በመበከል በዓለም ላይ ችግርንና ሞትን አመጣ። ብዙ ጊዜ እንደምንሰማው፡ "ወረርሽኝ መነሻው ላይ ብቻ አይወሰንም!" የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል መጥፎ ዜና ይነግረናል፡-

“ለሰዎችም አንድ ጊዜ መሞት ከእርሱ በኋላም ፍርድ እንደ ተመደበባቸው፥...
እነሆ፥ ጌታ በሁሉ ላይ እንዲፈርድ፥ በኃጢአተኝነትም ስላደረጉት ስለ ኃጢአተኛ ሥራቸው ሁሉ ዓመፀኞችም ኃጢአተኞች በእርሱ ላይ ስለ ተናገሩ ስለ ጭከና ነገር ሁሉ ኃጢአተኞችን ሁሉ እንዲወቅስ ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጥቶአል ብሎ ለእነዚህ ደግሞ ትንቢት ተናገረ።” (ዕብራውያን 9፥27 ይሁዳ 1፥15)

ስለዚህ፣ መጥፎው ዜና ሁላችንም ኃጢአተኞች ነን እናም የእግዚአብሔርን የጽድቅ ፍርድ መጋፈጥ አለብን! ይሁን እንጂ፣ መልካሙ ዜና (የምስራቹ) በዚያው በገነት ውስጥ፣ በምረቱ ባለጠጋ የሆነው እግዚአብሔር፣ አንድ ቀን ከድንግል የሚወለድን ኃጢአት የሌለበትን ሰው ወደ አለም እንደሚልክ ማስታወቁ ነው። ይህ ቅዱስ ሰው፣ ይህ ጻድቅ አዳኝ፣ ለአዳምና ለዘሮቹ ሁሉ ኃጢአት ለመክፈል ራሱን መስዋእት አድርጎ ይሞት ነበር። ለኛ የሚገባን የኃጢአት ቅጣት በዚህ ኃጢአት በሌለበት አዳኝ ላይ ይወድቃል። አዳምና ሔዋን ኃጢአት በሠሩበት ቀን እግዚአብሔር የሰበከው ወንጌል (የምስራች) ይህ ነው። እግዚአብሔር የዚህን አዳኝ መምጣት ለማወጅ ብዙ ሰዎችን ተጠቅሟል፣ እንዲሁም መሲህ ይባላል። እያንዳንዱ የእግዚአብሔር ነቢያት ስለ መሲሑ አንድ ነገር አውጀዋል፣ ስለዚህም እርሱ ሲመጣ እግዚአብሔር የሾመው እርሱ መሆኑን ሁሉም ይገነዘባል። ለምሳሌ ያህል፣ ከመሲሑ መምጣት ሰባት መቶ ዓመታት ቀደም ብሎ የነበረው ነቢዩ ኢሳይያስ፣ መሲሑ እንዴት እንደሚወለድ ተንብዮአል። "ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ማለት ነው።"( ማቴ. 1:23፤ ኢሳ. 7:14 ) ሚክያስ የተባለ ነቢይ ደግሞ መሲሁ ከሰማይ መጥቶ በቤተልሄም መንደር በምድር ላይ እንደሚወለድ ትንቢት ተናግሯል። በትክክል መሲሑ የተወለደበት ቦታ ይህ ነበር። ሆኖም ሚክያስ ይህን ትንቢት የተናገረው መሲሑ ከመወለዱ ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት ነው። ነገር ግን ነቢያት የመሲሑን መወለድ ብቻ አላወጁም። በተጨማሪም መሲሁ በኃጢአተኞች ምትክ መከራ እንደሚደርስበትና እንደሚምት ትንቢት ተናግረዋል። ለምሳሌ ነቢዩ ዳዊት ሰዎች መሲሑን እንደሚንቁት፣ እንደሚያሰቃዩት፣ እጁንና እግሩን እንደሚወጉ እና እንደሚገድሉት ጽፏል። ዳዊት የመሲሑን ሞት ማወጅ ብቻ ሳይሆን፣ እግዚአብሔር መሲሁን ከሞት እንደሚያስነሳውም ተንብዮአል፤ ይህም እግዚአብሔር የአዳምን ልጆች ከኃጢአት ቅጣት ለማዳን የላከው አንድና ብቸኛ አዳኝ መሆኑን አረጋግጣል።

ስለ መሲሁ መወለድ ብዙም ክርክር የለም፣ ነገር ግን ብዙዎች በሞቱና በትንሳኤው ይሰናከላሉ። ሰዎች የላከውን መሲህ ሲያዋርዱት እግዚአብሔር እንዴት ሊቆም እና ሊመለከት እንደሚችል አይገባቸውም። ብዙ ሰዎች ሊረዱት ያልቻሉት ነገር መሲሑ ለኃጢአታችን እንዲህ አይነት መከራ እንዲደርስበት ያቀደው እኛን የሚወደን አምላክ መሆኑን ነው። ነገር ግን ነቢያቱ እንዲህ ሲሉ አውጀዋል፡- “እግዚአብሔርም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።”
— (ኢሳይያስ 53፥10)

ነቢያትን እናምናለን? አዎ እናምናቸዋለን እንላለን። ነቢያትን በእርግጥ የምናምን ከሆነ የጻፉትንም ማመን አለብን። ነብያት የራሳቸውን ሃሳብ እንዳልተናገሩ ማስታወስ አለብን። እግዚአብሔር የሚናገሩትን በመንፈሳቸው ውስጥ አኖረ። እንግዲያውስ እነዚያን ነቢያት ለማመን ብንቃወም፣ ማንን ነው ምንቃወመው? የምንቃወመው እግዚአብሔርን ነው። ምክንያቱም ነቢያት መሲሁ ኃጢአትን ለማስወገድ መስዋዕት ሆኖ እንደሚሞት ትንቢት እንዲተነብዩ ያነሳሳው እርሱ ነውና።

{የሚቀጥለው ማሊክ የሚባል ሰው የግል ምስክርነት ነው።} እዚህ ጋር ቆም ላድርገውና እንዴት በኢየሱስ ክርስቶስ አማኝ እንደሆንኩ ልንገራችሁ። በወጣትነቴ በቀን አምስት ጊዜ ለመጸለይ እና አመታዊ ጾምን ለመጾም ታማኝ ነበርኩ፣ ነገር ግን ከሞትኩ በኋላ ወዴት እንደምሄድ አላውቅም ነበር። ዙሪያዬ ያሉትን ሁሉ ጠየኩ፣ ሆኖም ግልጽ የሆነ መልስ አላገኘሁም። ወንጌልን (ኢንጂልን) ሳጠና ግን፣ ከሞቴ በኋላ ወዴት እንደምሄድ ማወቅ እንደምችል አወቅሁ፤ ምክንያቱም መሲሁ ኢየሱስ ራሱ በወንጌል እንዲህ ይላል፦ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፥ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም።” (ዮሐንስ 5፥24) እንዲሁም እንዲህ ብሏል፦ “ኢየሱስም፦ ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤” (ዮሐንስ 11፥25) ስለዚ፣ ራሴን ለማዳን ከራሴ ጥረት ንስሃ ገብቼ ነቢያት ሁሉ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ በስሙ የኃጢአቱን ስርየት ይቀበላል" ብለው ትንቢት በተናገሩለት መሲህ አመንኩኝ (ሐዋርያት 10፥43)። ተስፋዬን ሁሉ ወስጄ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ አስቀመጥኩት። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔር ለመንፈሴ ሰላም አምጥቶላታል። አሁን ህሊናዬ አይረበሽም። ኢየሱስ በመስቀል ላይ ከሰራው ሥራ የተነሳ የወደፊት እጣዬ በሚያስደንቅ ሁኔታ ብሩህ ነው። በሕይወቴ እንደ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር፣ አንዳንድ ጊዜ ችግር እና መከራ ያጋጥመኛል ምክንያቱም እምነቴ ከዘመዶቼ እና ከጓደኞቼ አስተያየት ስለሚለያይ፤ ግን ሰላም አለኝ። የእግዚአብሔር ሰላም ልቤንና አእምሮዬን ሞልቶታል። ይህን የሰጠኝ ኢየሱስም እንዲህ ይላል፦ “ዓለም ቢጠላችሁ ከእናንተ በፊት እኔን እንደ ጠላኝ እወቁ።” (ዮሐንስ 15፥18) “ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም።” (ዮሐንስ 14፥27) እና ወዳጆች ሆይ፣ ጌታ ለእኔ እና በእኔ ያደረገውን ለእያንዳንዳችሁ ሊያደርግ ይችላል። ካንተ ወይም ካንቺ አንድ ነገር ይጠይቃል፡-ሙሉ ልብህን እንድትሰጠው። ሙሉ ልብሽን እንድትሰጪው። የቀረውን እሱ ያደርገዋል። ጌታ ኢየሱስ ራሱ እንዲህ ብሏልና። "እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤" (ማቴ. 11:28-29)

እግዚአብሔር ታላቁን ማዳኑን መቼም ቢሆን አይሸጥልህም ወይም አይሸጥልሽም። እንዲሁ ያለ ምንም ዋጋ (ከእናንተ ባልሆነ ዋጋ) በነጻ ሊሰጣችሁ ነው ሚፈልገው። መልካም ስራ፣ ፀሎት (ሶላት) እና ፆም በውስጣችሁ ጥሩ ስሜት ይሰጡ ይሆናል፣ ነገር ግን የእግዚአብሔርን ፅድቅ አያረኩም! ወደ እግዚአብሔር ገነት የምትገባበት/የምትገቢበት መንገድ አንድ ብቻ ነው።

1.) በመጀመሪያ ኃጢአተኛ እንደሆንክና አምላክን ለማስደሰት የሚያስችል ኃይል እንደሌለህ መገንዘብ ይኖርብሃል።

2.) ከዚያም ኢየሱስ ክርስቶስ አዳኝ እንደሆነ፣ ኃጢአትህን ለማስወገድ እግዚአብሔር በመስቀል ላይ እንዲሞት እንደ ላከውና እግዚአብሔር የዘለአለም ሕይወትን ይሰጥህ ዘንድ እንዳስነሳው ማመን አለብህ።

የኦሮምኛውን ቻናሌን ለማግኘት ይህንን ተጫኑ👇
   / @dhugaanniboqachiisa  

አስተያየታችሁን በውስጥ ማድረስ የምትፈልጉ ይህንን የቴሌግራም ሊንክ ተጠቀሙ👇
http://t.me/BibleAndMe
Additional: - ewnetyasarfal123@gmail.com

አላህን ፈለኩት ኢየሱስን አገኘሁት ምስክርነት ||ከእስልምና ወደ ክርስትና || Nabeel Qureshi Amharic

Поделиться в:

Доступные форматы для скачивания:

Скачать видео mp4

  • Информация по загрузке:

Скачать аудио mp3

Похожие видео

እውነት የክርስቲያኖች አምላክ ሶስት ነው ወይስ አንድ፣ መልአክ ክንፍ ያለው ፍጡር... || Al Fadi, David Wood, Sam Shamoun Amharic

እውነት የክርስቲያኖች አምላክ ሶስት ነው ወይስ አንድ፣ መልአክ ክንፍ ያለው ፍጡር... || Al Fadi, David Wood, Sam Shamoun Amharic

ከእስልምና ወደ ክርስትና የመሐመድ ፋሪዲ ነጻ የወጣበት አስደናቂ ምስክርነት || Leaving Islam for Christianity

ከእስልምና ወደ ክርስትና የመሐመድ ፋሪዲ ነጻ የወጣበት አስደናቂ ምስክርነት || Leaving Islam for Christianity

#አትወቅ//ሁሉም ሰው ሊያየው የሚገባ የእግዚአብሔር ቃል ትምህርት//SCGC//

#አትወቅ//ሁሉም ሰው ሊያየው የሚገባ የእግዚአብሔር ቃል ትምህርት//SCGC//

ትራምፕ ስለዐቢይ “አላውቀውም ጠንካራ”፣ መከላከያ “የካዳቸው ሚሊሻዎች”፣ ጄኔራሉ ስለጎጃም ዘመቻ፣ የታዬዎች ውሎ፣  ስለፓትሪያርኩ ጤንነት ምላሽ | EF

ትራምፕ ስለዐቢይ “አላውቀውም ጠንካራ”፣ መከላከያ “የካዳቸው ሚሊሻዎች”፣ ጄኔራሉ ስለጎጃም ዘመቻ፣ የታዬዎች ውሎ፣ ስለፓትሪያርኩ ጤንነት ምላሽ | EF

መንፈስ ቅዱስ  ከናንተ ጋር መሆኑን እንዴት ታውቃላችሁ? ብቻህን ሁን! ኢየሱስን አጥናው! Relationship with the Holy Spirit!

መንፈስ ቅዱስ ከናንተ ጋር መሆኑን እንዴት ታውቃላችሁ? ብቻህን ሁን! ኢየሱስን አጥናው! Relationship with the Holy Spirit!

እንደ አጵሎስ አትሁኑ | @1BibleAnswers

እንደ አጵሎስ አትሁኑ | @1BibleAnswers

ሙስሊሞችን ወደ ክርስትና እንዳይመጡ የሚያደርጋቸው ነገር ምንድነው? Nabeel Qureshi Amharic

ሙስሊሞችን ወደ ክርስትና እንዳይመጡ የሚያደርጋቸው ነገር ምንድነው? Nabeel Qureshi Amharic

የአህመድ ሙሐመድ ያሁኑ #ገብረስላሴ የክርስትና ጉዞ!

የአህመድ ሙሐመድ ያሁኑ #ገብረስላሴ የክርስትና ጉዞ!

አስገራሚ ምስክርነት ከአሸባሪንት አንስቶ ሰው አርገው በእንባ እያለቀሰ ከ17 ዓመታት በፊት ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረገለት አካፍሏል | Amazing testm!!!

አስገራሚ ምስክርነት ከአሸባሪንት አንስቶ ሰው አርገው በእንባ እያለቀሰ ከ17 ዓመታት በፊት ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረገለት አካፍሏል | Amazing testm!!!

ተውሂድ ወይስ ሥላሴ || እስልምና ወይስ ክርስትና || ትክክለኛው የቱ ነው? Dr. Shabir Ally and Dr. Nabeel Qureshi Debate ክፍል 2

ተውሂድ ወይስ ሥላሴ || እስልምና ወይስ ክርስትና || ትክክለኛው የቱ ነው? Dr. Shabir Ally and Dr. Nabeel Qureshi Debate ክፍል 2

#ራህ አብዱልሀሚድ የግብጻዊቷ ድንቅ ምስክርነት/#pastor Gezai Yohannes El Shaddai

#ራህ አብዱልሀሚድ የግብጻዊቷ ድንቅ ምስክርነት/#pastor Gezai Yohannes El Shaddai

የመሐመድ የዘር ግንድ ውስጥ ነኝ፣ ከእስልምና በመውጣቴ የግድያ ሙከራ ተደርጎብኛል

የመሐመድ የዘር ግንድ ውስጥ ነኝ፣ ከእስልምና በመውጣቴ የግድያ ሙከራ ተደርጎብኛል

🔴ክርስቶስን አገኘሁት | እውነተኛ ታሪክ | አክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና ክፍል 1 | Islam encounters Christ  part 1#bible#new

🔴ክርስቶስን አገኘሁት | እውነተኛ ታሪክ | አክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና ክፍል 1 | Islam encounters Christ part 1#bible#new

መሐመድን የገደለው ማን ነው? 10 ምክንያቶች || Who Killed Muhammad? [David Wood Amharic]

መሐመድን የገደለው ማን ነው? 10 ምክንያቶች || Who Killed Muhammad? [David Wood Amharic]

እውነታው ወጣ |የሙሀ*መድ አባት ራሱ..​⁠♦️[ክፍል2️⃣] ሌሊቱን ሁሉ ቁር**ዓን እየቀራው…@abdo_jaro| #PistisPodcast #ኢየሱስ

እውነታው ወጣ |የሙሀ*መድ አባት ራሱ..​⁠♦️[ክፍል2️⃣] ሌሊቱን ሁሉ ቁር**ዓን እየቀራው…@abdo_jaro| #PistisPodcast #ኢየሱስ

የቀድሞው ከድር ከማል ያሁኑ ገብረ ሩፋኤል ምስክርነት ከእስልምና ወደ ክርስትና!{የአብርሃም መንገድ አንድ}

የቀድሞው ከድር ከማል ያሁኑ ገብረ ሩፋኤል ምስክርነት ከእስልምና ወደ ክርስትና!{የአብርሃም መንገድ አንድ}

‘መሀመድ የ6 ዓመት ልጅ ማግባቱ ለህሊናዬ እስካሁን እረፍት አይሰጠኝም' ||Mohammed abebaw(መሐመድ አበባው) || #Meskelmedia#2025

‘መሀመድ የ6 ዓመት ልጅ ማግባቱ ለህሊናዬ እስካሁን እረፍት አይሰጠኝም' ||Mohammed abebaw(መሐመድ አበባው) || #Meskelmedia#2025

የራውዳ ኣስደናቂ የህይወት ምስክርነት፡

የራውዳ ኣስደናቂ የህይወት ምስክርነት፡ "ኢየሱስ ከሁሉ ይበልጣል" Rawda Testimony

ብዙ ሙስሊሞች ክርስትናን እንዲቀበሉ ምክንያት የሆነው የአረብ ሙስሊም // Al Fadi Amharic

ብዙ ሙስሊሞች ክርስትናን እንዲቀበሉ ምክንያት የሆነው የአረብ ሙስሊም // Al Fadi Amharic

ተውሂድ ወይስ ሥላሴ || እስልምና ወይስ ክርስትና || ትክክለኛው የቱ ነው? Dr. Shabir Ally and Dr. Nabeel Qureshi Debate ክፍል 1

ተውሂድ ወይስ ሥላሴ || እስልምና ወይስ ክርስትና || ትክክለኛው የቱ ነው? Dr. Shabir Ally and Dr. Nabeel Qureshi Debate ክፍል 1

© 2025 dtub. Все права защищены.

  • Контакты
  • О нас
  • Политика конфиденциальности

Контакты для правообладателей: infodtube@gmail.com