Ethiopian Doro Wot ዶሮ ወጥ
Автор: Melegna | መለኛ
Загружено: 2025-01-05
Просмотров: 111791
ዶሮ ወጡን ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉን ግብዓቶች እና የማጣፈጫ ቅመሞች አይነት እና መጠን
ይህ ከስር የተዘረዘረው የግብዓት መጠን ለ2 ዶሮ የሚሆን ነው
4ኪሎ ቀይ ሽንኩርት
ሽንኩርቱ ቶሎ እንዲበስል እንዲሁም ፈጦ እንዳይታይ በከፊል ላም አድርጋችሁ መፍጨት ይኖርባቹሃል
ግማሽ ኩባያ የምግብ ዘይት
ዘይት ያሳነስንበት ምክንያት ሽንኩርቱን በደንብ በብስል ቂቤ ስለምናቁላላው ነው ፡፡ ብስል ቂቤ ከሌላችሁ የዘይቱን መጠን ከፍ አድርጋችሁት በዘይት ብቻ ማብሰል ይቻላል ፡፡
3 የሾርባ ማንኪያ ብስል ቂቤ
3 ከግማሽ ከኩባያ በርበሬ
የምትጨምሩት የበርበሬ መጠን እንደ በርበሬያችሁ አይነት ይወሰናል ፡፡ ሁላችን ቤት የሚገኘው የበርበሬ አይነት ሊለያይ ስለሚችል ትንሽ ትንሽ እየጨመራችሁ መጥኑ፡፡
ግማሽ ኩባያ የተፈጭ ነጭ ሽንኩርት
2 የሾርባ ማንኪያ የማቁላያ ቅመም
1 የሾርባ ማንኪያ የኮረሪማ ዱቄት
የፈላ ውሃ
የፈላውሃውን ቁሌቱን ለማላላት እንዲሁም ወጡ ላይ ለመከለስ እንጠቀመዋለን
1 የሾርባ ማንኪያ የመከለሻ ቅመም
2 የሾርባ ማንኪያ ለጋ ቂቤ
2 ተገንጥሎ በደንብ የታጠበ ዶሮ
12 የተቀቀለ እንቁላል
ማባያ
እንጀራ
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: