የሕዳር 13 ሥንክሳር
Автор: kesisephrem
Загружено: 2025-11-21
Просмотров: 103
ስንክሳር ዘወርኀ ኅዳር 13
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ኅዳር ዐሥራ ሦስት በዚች ቀን የአእላፍ መላእክትን የበዓላቸውን መታሰቢያ እናደርግ ዘንድ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙን ። እሊህም ሥጋ የሌላቸው ረቂቃን የሆኑ ለዓለሙ ሁሉ የሚማልዱ ናቸው ።
ኄኖክም ስለእርሳቸው እንዲህ አለ በሰማይ እያለሁ ነፋሳት በደመና ውስጥ አወጡኝ በእሳት ላንቃም ወደታነፀ ቤት አደረሱኝ በዚያም አእላፋት መላእክትን አየሁ እነርሱም በእሳት ላቦት ላይ የቆሙ ልብሳቸውም እንደ በረድ ነጭ ነው አለ ።
ያዕቆብም እንዲህ አለ ከምድር እስከ ሰማይ የምትደርስ መሰላልን አየሁ የእግዚአብሔርም መላእክት በውስጥዋ ይወጡ ይወርዱ ነበር ። ሁለተኛም ከሶርያ መመለሻው በሆነ ጊዜ የመላእክት ሠራዊትን አየሁ አለ ።
ሙሴም እንዲህ አለ እግዚአብሔር አሕዛብን በቦታ እንደለያቸው የአዳምን ልጆች እንደበተናቸው እግዚአብሔርን በሚያገለግሉ መላእክት ቁጥርየአሕዛብን አውራጃዎች እንደ ወሰናቸው ። ሁለተኛም እግዚአብሔር ከሲና ተራራ መጥቶ በሴይር ታየኝ ረቂቃን መላእክቶቹም ከእርሱ ጋር ነበሩ አለ ።
ዳዊትም እንዲህ አለ መላእክቱን መንፈስ አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል የሚያደርግ እርሱ ነው ። ሁለተኛም የእግዚአብሔር ሠረገላዎች የብዙ ብዙ ሽህ ናቸው አለ ። ኤልሳዕም የእሳት ሠረገሎችና የእሳት ፈረሶች በዙሪያው ቁመው ሲጠብቁት አየ ።
ዳንኤልም እንዲህ አለ ዙፋኖችን እስቲዘረጉለት ድረስ ደርሶ አየሁ ብሉየ መዋዕል እግዚአብሔር በላያቸው ተቀመጠ ልብሱም እንደ በረድ ነጭ ነው የራሱም ጠጉር እንደ ብዝት ነጭ ነው ዙፋኑም የሚነድ እሳት ነው ሠረገላውም የሚንቦገቦግ ፍም ነው ። የእሳትም ጐርፍ በፊቱ ይፈሳል የብዙ ብዙ የሆኑ መላእክትም ያገለግሉታል የእልፍ እልፍ መላእክትም በፊቱ ይቆማሉ በአደባባይም ተቀምጦ መጻሕፍትን ገለጠ ።
ሉቃስም እንዲህ አለ ድንገትም ከዚያ መልአክ ጋር ብዙ የሰማይ ሠራዊት መጡ እግዚአብሔርንም ሲያመሰግኑ በሰማይ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በምድርም ሰላም ለሰው ልጅ በጎ ፈቃድ እያሉ ።
ማቴዎስም እነሆ መላእክትም ሊአገለግሉት መጡ አለ ። ሁለተኛም የሰው ልጅ ቅዱሳን መላእክትን አስከትሎ በጌትነቱ በሚመጣበት ጊዜ ያን ጊዜ በጌትነቱ ዙፋን ላይ ይቀመጣል ። ዮሐንስም ጌታችን ከተናገረው ቃል እንዲህ አለ እውነት እውነት እላችኋለሁ ከእንግዲህ ወዲህ ሰማዮች ሲከፈቱ የእግዚአብሔርም መላእክት ወደ ሰው ልጅ ሲወርዱና ሲወጡ ታያላችሁ አላቸው የሚል ነው ።
ሐዋርያው ይሁዳም እነሆ እግዚአብሔር ይፈርድ ዘንድ አእላፋት የሆኑ ቅዱሳን መላእክቶቹን አስከትሎ ይመጣል አለ ። የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትም የመዓርጋቸውን ደረጃ ወይም አይነት እንዲህ ብለው ተናገሩ መላእክት አጋዕዝት ሥልጣናት ኃይላት መናብርት መኳንንት ሊቃናት አርባብ ኪሩቤል ሱራፌል ብለው ተናገሩ ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በእሊህ በቅዱሳን መላእክቶቹ አማላጅነት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን ።
በዚችም ቀን ዐሥራ ሦስት ወንበዴዎች ስለርሱ በእርሱ ሃይማኖት ከዓለም የተለዩ የከበረ ባለጸጋ አስከናፍር አረፈ ። ይህም አስከናፍር ከሮሜ መኳንንት አንዱ ነው እርሱም ለድኆችና ለምስኪኖች ምጽዋትን የሚሰጥ እንግዶችንና መጻተኞችን የሚቀበል ነው ።
በዚያም ወራት ያገኙትን ሰው ሁሉ የሚነጥቁና የሚያጠፉ ዐሥራ ሦስት ሽፍቶች ነበሩ እንግዳ እንደሚቀበል ይልቁንም መነኰሳትን እንደሚወድ የአስከናፍርን ዜና በሰሙ ጊዜ ወደርሱ ሒደው በተንኮል ይገድሉት ዘንድ ገንዘቡንም ሁሉ ሊወስዱ ተማከሩ ። ከዚህም በኋላ የምንኲስና ልብስ ለብሰው ከደጁ ቆሙ በአያቸውም ጊዜ ዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት እንደሆኑ አንዱ ጌታ ክርስቶስ እንደሆነ አሰበ ሰገደላቸውም ወደ ቤቱም አስገብቶ ማዕድ አቀረበላቸው እግራቸውንም አጠበ ሠላሳ አምስት ዓመት ሽባ ሆኖ በኖረ ልጁ ላይ ያንን እግራቸውን የታጠቡበትን ውኃ ረጨ ወዲያውኑ ልጁ ዳነ ።
እነዚያ ሽፍቶችም የሆነውን በአዩ ጊዜ እጅግ ደነገጡ እርሱ አስከናፍር ግን አባቶቼ ሆይ ጌታ ክርስቶስ ከእናንተ መካከል የቱ እንደሆነ ንገሩኝ እሰግድለት ዘንድ አላቸው የአገር ሰዎችም የመኰንኑ ልጅ እንደዳነ በሰሙ ጊዜ ወደርሳቸው መጥተው ሰገዱላቸው እንዲህም አሏቸው የእግዚአብሔርቅዱሳኖች ሆይ ባርኩን በሽተኞቻችንን አድኑልን ። ከዚህም በኋላ እሊያ ወንበዴዎች ሾተሎቻቸውን አውጥተው በእርሳቸው ልንገድልህ በወደድንበት እኛን ይገድሉን ዘንድ እሊህን ሾተሎች ውሰድ አሉት እግዚአብሔር በአንተ ጽድቅ የራራልን ባይሆን በአጠፋን ነበር ።
ይህንንም ከአሉት በኋላ ተሰናበቱት ከእርሱም አንድ አንድ መስፈሪያ ምስርለየአንዳንዳቸው ተቀብለው ሃያ አምስት ቀን ያህል የሚያስጉዝ ጉዳና ወደ
ምድረ በዳ ተጓዙ ያንንም ምስር ከአሸዋ ውስጥ በተኑት ፀሐይ በሚገባም ጊዜ ከአሸዋው ውስጥ ሦስት ሦስት ምስር ፈልገው ይቀምሳሉ እንደዚህም ሠላሳ ዓመት ኖሩ ። ከዚህም በኋላ ከሀዲ መኰንን በመጣ ጊዜ እርሱ ወዳለበት ሒደው በጌታችን ታመኑ እርሱም ገደላቸውና የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበሉ
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአስከናፍርና በእሊህ ቅዱሳን ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን ።
በዚችም ቀን የሀገረ እንጽና ኤጲስቆጶስ የከበረ አባት ጢሞቴዎስ አረፈ ። ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ ጀምሮ ልቡ ንጹሕ የሆነ ጻድቅ ሰው ነው ታላቅ ተጋድሎንም የተጋደለ ነው ። የእንጽና አገር መኰንንም ለሰዎች የቀናች ሃይማኖትን በማስተማሩና በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ አመነ ይዞ ጽኑዕ ሥቃይን ብዙ ዘመናት አሠቃየው ። ከእሥር ቤትም አውጥቶ ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃይቶ ወደ እሥር ቤት ይመልሰው ነበርከእርሱም ጋር ስለ ሃይማኖት የታሠሩ ብዙዎች ቅዱሳን ሰማዕታት ነበሩ ከእሳቸውም በወህኒ ቤት ጥቂቶች እስከቀሩ ድረስ ያ ከሀዲ መኰንን ብዙዎቹን አውጥቶ አሠቃይቶ ንጹሕ ደማቸውን በማፍሰስ ፈጃቸው
በዚችም ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ስልሳ አራተኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት ዘካርያስ አረፈ ። ይህም አባት ከእስክንድርያ ሰዎች ወገን ነው በቤተ ክርስቲያንም ንብረት ሁሉ ላይ መጋቢነትና ቅስና ተሾመ እርሱም በተጋድሎ የጸና ንጹሕ ድንግል ነው በጠባዩም የዋህ ቅን የሆነ በዕድሜውም የሸመገለ ነው ።
ሊቀ ጳጰሳት አባ ፊላታዎስም በአረፈ ጊዜ ለዚች ሹመት የሚገባ ሰው ይመርጡ ዘንድ በእግዚአብሔር ምክር ኤጲስቆጶሳት ተሰበሰቡ እነርሱም ለዚች ሹመት ስለሚሻል ሰው በወንጌላዊ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ተሰብስበው እየተነጋገሩ ሳሉ እነሆ አንድ ሰው መማለጃ በመስጠት ያለ ኤጲስቆጶሳት ፈቃድ ሊቀ ጵጵስና ይሾሙት ዘንድ ከንጉሥ የመልእክት ደብዳቤ ይዞ እንደሚመጣ ከእርሱም ጋር ከንጉሥ የተቀበላቸው ጭፍሮች እንዳሉ ሰሙ ።
ኅዳር ፲፫ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.አእላፍ ፱፱ኙ ነገደ መላእክት
፪.ቅዱስ አስከናፍር ሮማዊ
፫.፲፫ቱ ግኁሳን አበው ሽፍቶች የነበሩ
፬.ቅዱስ ጢሞቴዎስ ዘእንጽና
፭.አባ ዘካርያስ ሊቀ ዻዻሳት
ወርኀዊ በዓላት
፩.እግዚአብሔር አብ
፪.ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላዕክት
፫.ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ ገዳማዊ
፬.አቡነ ዘርዐ ቡሩክ
ስለ መላእክትም ፦ መላእክቱን መናፍስት: አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል የሚያደርግ ይላል ፤ ስለ ልጁ ግን አምላክ ሆይ ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል ፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው ። ጽድቅን ወደድህ ዓመጽንም ጠላህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ ከጓደኞችህ ይልቅ በደስታ ዘይት ቀባህ ይላል ። . . .ነገር ግን ከመላእክት ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ ከቶ ለማን ተብሏል? ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን? ዕብ. ፩፥፯-፲፬
@እናታችንማርያምሆይእንወድ @kesishenokweldemariam2240 @EfoyZeOrthodox
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: