Популярное

Музыка Кино и Анимация Автомобили Животные Спорт Путешествия Игры Юмор

Интересные видео

2025 Сериалы Трейлеры Новости Как сделать Видеоуроки Diy своими руками

Топ запросов

смотреть а4 schoolboy runaway турецкий сериал смотреть мультфильмы эдисон
dTub
Скачать

ጋብቻ በግል ንብረት ላይ የሚያስከትለው ውጤት

Автор: Lawyer kidist Elias

Загружено: 2025-03-05

Просмотров: 1012

Описание:

#ጋብቻ በንብረት በኩል ምን ዓይነት ውጤት አለው?
=============
ጋብቻ በ #ባልና #ሚስት መካከል ራሱን የቻለ ግንኙነት የሚፈጥር ከመሆኑ አንፃር በመካከላቸው ያለውን ግላዊ ግንኙነትም ሆነ በንብረት ረገድ የሚኖራቸውን ግንኙነት በጋብቻ ውል መስማማት የሚችሉ ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ ይደነግጋል(አንቀፅ 42)፡፡ የጋብቻ ውል ማለት ባልና ሚስት ጋብቻቸው ንብረታቸውን በተመለከተ ስለሚያስትለው ውጤት እንዲሁም ግላዊ ግንኙነታቸውን በተመለከተ ስለሚኖራቸው መብቶችና ግዴታዎች ጋብቻቸውን ከመፈፀማቸው በፊት ወይም እጅግ ቢዘገይ ጋብቻቸውን በሚፈፅሙበት ዕለት የሚያደርጉት ስምምነት ነው፡፡ ይሁንና ባልና ሚሰት ይህንን ግንኙነታቸውን ለመወሰን ያደረጉት ውል የሌለ እንደሆነ ይህ አይነቱ ግንኙነት በህጉ በተቀመጡ ድንጋጌዎች የሚገዛ ይሆናል፡፡

በጋብቻ ውስጥ ያለ #ንብረት የግል ሀብት አሊያም የጋራ ሀብት ሊሆን ይችላል፡፡ በመርህ ደረጃ አንደኛው ተጋቢ የግል ሀብቱ መሆኑን ካላስረዳ በስተቀር ንብረቱ በባል ወይም በሚስት ስም ብቻ የተመዘገበ ቢሆንም እንኳን ንብረቱ የጋራ ሀብት እንደሆነ ህጉ ግምት /#Legal Presumption/ ይወስዳል፡፡ (አንቀፅ 63(1))፡፡ ምንም እንኳን የህጉ ግምት በትዳር ውስጥ ያለ ማንኛውም ንብረት የጋራ ንብረት ነው የሚል ቢሆንም ተገቢዎች ንብረቱ የግላቸው መሆኑን ማስረዳት እሰከቻሉ ጊዜ ድረስ ጋብቻው ፀንቶ ባለበት ሁኔታም ባልና ሚስት የየራሳቸው የግል ንብረት ሊኖራቸው የሚችል ስለመሆኑ ከህጉ መገንዘብ ይቻላል፡፡

ጋብቻ ከመመስረቱ አስቀድሞ ተጋቢዎች በየግላቸው የነበራቸው ንብረት እንደ ጋራ ንብረት ይቆጠራል ወይስ አይቆጠርም የሚል ጥያቄ ብዙ ጊዜ ይስተዋላል፡፡ባልና ሚሰት ከጋብቻ በፊት የነበራቸውን የግል ንብረት የጋራ ሀብት እንዲሆን መደንገጉ ምን አይነት አንድምታ ሊኖረው እንደሚችል ከግምት ውስጥ በማስገባት የኢፌድሪ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ ሀተታ ዘ-ምክንያት እንዲህ ይገልፀዋል…

“ተጋቢዎች ከጋብቻ በፊት የነበራቸውን የግል ንብረት የጋራ ሀብት እንዲሆን መደንገጉ ጋብቻን ከንብረት ጋር የማየት ሁኔታና አስተሳሰብ የሚፈጥር ሲሆን በውጤቱም ጋብቻ ሀብት ለመካፈል የመፈፀምበትና የሚፈርስበት ዕድል ይከፍታል፡፡ምንም ያልነበረው ተጋቢ ንብረት ያለውን ሰው ብቻ በማግባት ጋብቻው ሲፈርስ የሚካፈልበትን ሁኔታ በሕጋዊ አስተዳዳር ስር ማስቀመጡ በሕሊናም ሆነ በፍትህ ረገድ ተቀባይነት የሚኖረው አይደለም፡፡” 

ይህንን ሀሳብ መነሻ በማድረግም የቤተሰብ ህግ በአንቀፅ 57 እና 58 የባልና ሚስት ሀብትን ያለግብይት የተገኙ የግል ንብረቶችና በግብይት የተገኙ የግል ንብረቶች በሚል ከፋፍሎ አስቀምጧል።

ከቤተሰብ ህጉ አንቀፅ 42 እና 58 የጣምራ ንባብ መረዳት እንደሚቻለው ባልና ሚስት በጋብቻ ውላቸው ያደረጉት ሌላ ተቃራኒ ስምምነት ከሌላቸው በስተቀር  ከጋብቻ በፊት በየግል የነበራቸው ንብረት እንዲሁም ከጋብቻ በኃላ በውርስ አሊያም በስጦታ በየግል ያገኟቸው ንብረቶች የግላቸው ሆነው የሚቀሩ ናቸው።

ይሁን እንጂ ባልና ሚስት ጋብቻ ከመሰረቱ በኋላ አንዱ በግሉ የነበረውን የግል ሀብት ቢለውጥ ወይም ይህንን ንብረት ሸጦ ሌላ ቢገዛ ወይም ይህንን ንብረት ሸጦ ገንዘቡን ቢይዝ የግል ይባልልኝ ብሎ ለፍርድ ቤት ጥያቄ አቅርቦ ካላፀደቀው በቀር ይህ ንብረት የጋራ የሚሆን ስለመሆኑ ህጉ በግልፅ ይደነግጋል። ይህም ማለት ለምሳሌ ጋብቻ ውስጥ ከመግባቱ በፊት ባል መኪና ቢኖረው እና ይህንን መኪና ትዳር ውስጥ ከገባ በኋላ ቢሸጠው ወይም ከሌላ ሰው ጋር በሌላ ንብረት ቢለዋወጥ አሊያም መኪናውን ሸጦ ገንዘቡን በእጁ ቢይዝ ይህንን መሰረት አድርጎ በግብይት የተገኘው ንብረት የግል ይባልልኝ ብሎ ፍርድቤት ቀርቦ ጥያቄ እስካላቀረበና ፍርድቤቱ እስካላፀደቀው ጊዜ ድረስ ንብረቱ የባልና ሚስት የጋራ ንብረት ይሆናል(አንቀፅ 58)።

በሌላ በኩል በህጉ የባልና ሚስት የጋራ ንብረት ተደርጎ የሚውሰደው ባልና ሚስት ከግል ጥረታቸው የሚያገኙት እና ከግል እና ከጋራ ንብረት የሚያገኟቸው ንብረቶች ናቸው።ይኸውም ከቅጥር የሚገኝ ደመወዝ፣ከባልና ሚስት የግል ንብረት የሚገኝ ገቢ(ለአብነትም ከላይ በቀረበው ምሳሌ ባል የግል በሆነው መኪና ገቢ የሚያስገኝ ስራ ላይ ቢሰማራ ወይም የግል ቤት ቢኖረው ቤቱን ከማከራየት የሚያገኘው ገቢ)፣ በትዳራቸው ካፈሩት የጋራ ንብረት የሚገኘው ገቢ እንዲሁም ከላይ በተገለፀው አግባብ በግብይት የተገኘው ንብረት የግል ስለመሆኑ ፍርድቤት ካላፀደቀው የባልና ሚስት የጋራ ሀብት ነው(አንቀፅ 62)።
---------------------------------------
የገጠማችሁ እና የህግ ምክር የምትፈልጉበት ማንኛውም ጉዳይ ካለ በኮመንት መስጫው ስር የሚገኘውን የመወያያ ግሩፓችንን በመቀላቀል ጥያቄ ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡👇🏽👇🏽

ለበለጠ፡ contact us
☎️0925122319
tiktok.com/@lawyer_kidist_elias
telegram @kidistelias

ጋብቻ በግል ንብረት ላይ የሚያስከትለው ውጤት

Поделиться в:

Доступные форматы для скачивания:

Скачать видео mp4

  • Информация по загрузке:

Скачать аудио mp3

Похожие видео

የጋብቻ ውል አፈጻጸም እና ውጤቶቹ!!  ፍች እንዴት እንደሚፈጸምና የፍች ውጤቶች..... | Marriage | Divorce

የጋብቻ ውል አፈጻጸም እና ውጤቶቹ!! ፍች እንዴት እንደሚፈጸምና የፍች ውጤቶች..... | Marriage | Divorce

ጋብቻ በተጋቢዎች ንብረት ላይ ስለሚኖረው የሕግ ውጤት

ጋብቻ በተጋቢዎች ንብረት ላይ ስለሚኖረው የሕግ ውጤት

Samri YouTube ሳምሪ ዩቱብ  is live እንኳን አደረሳቹ ለብርሃነ ጥምቀቱ#

Samri YouTube ሳምሪ ዩቱብ is live እንኳን አደረሳቹ ለብርሃነ ጥምቀቱ#

Суҳроб Одилиён кист? қисми 2

Суҳроб Одилиён кист? қисми 2

⚡️ Трампа встретили матом || Дерзкое заявление Зеленского

⚡️ Трампа встретили матом || Дерзкое заявление Зеленского

ህግን በአዲስ እይታ || ባል እና ሚስት || የግል እና የጋራ ንብረት

ህግን በአዲስ እይታ || ባል እና ሚስት || የግል እና የጋራ ንብረት

#EBC የህግ ነገር ጋብቻ ሳይፈጸም  እንደባል እና ሚስት አብሮ መኖር በህጉ ያለው ጥበቃ ክፍል 1

#EBC የህግ ነገር ጋብቻ ሳይፈጸም እንደባል እና ሚስት አብሮ መኖር በህጉ ያለው ጥበቃ ክፍል 1

ደማቁ የእከ (የአርቲስት ንብረት ገላው) ሰርግ ወንድማችን እግዚአብሔር ትዳርህን ይባርክ!

ደማቁ የእከ (የአርቲስት ንብረት ገላው) ሰርግ ወንድማችን እግዚአብሔር ትዳርህን ይባርክ!

ПОСЛЕ СМЕРТИ ВАС ВСТРЕТЯТ НЕ РОДСТВЕННИКИ, А.. ЖУТКОЕ ПРИЗНАНИЕ БЕХТЕРЕВОЙ. ПРАВДА КОТОРУЮ СКРЫВАЛИ

ПОСЛЕ СМЕРТИ ВАС ВСТРЕТЯТ НЕ РОДСТВЕННИКИ, А.. ЖУТКОЕ ПРИЗНАНИЕ БЕХТЕРЕВОЙ. ПРАВДА КОТОРУЮ СКРЫВАЛИ

ጋብቻ በንብረት ላይ የሚያስከትለው ውጤት፡፡ የጋራና የግል ሀብት ምን ምን ናቸው? #seyfu_on_ebs #habeshatiktok #ጋብቻ እና ንብረት

ጋብቻ በንብረት ላይ የሚያስከትለው ውጤት፡፡ የጋራና የግል ሀብት ምን ምን ናቸው? #seyfu_on_ebs #habeshatiktok #ጋብቻ እና ንብረት

ከ100 ብር በላይ ባልና ሚስት ካልተስማሙ አንዱ ወገን ብቻ ስጦታ መስጠት አይችልም፤ ጋብቻና ንብረትን በተመለከተ ህጉ ምን ይላል... ? #ዳኝነት

ከ100 ብር በላይ ባልና ሚስት ካልተስማሙ አንዱ ወገን ብቻ ስጦታ መስጠት አይችልም፤ ጋብቻና ንብረትን በተመለከተ ህጉ ምን ይላል... ? #ዳኝነት

#ጋብቻ፣ፍቺ እና የንብረት ክፍፍል  በተመለከተ በአቶ ገድለሰላም ተክሉ የቀረበ አጭር ማብራሪያ

#ጋብቻ፣ፍቺ እና የንብረት ክፍፍል በተመለከተ በአቶ ገድለሰላም ተክሉ የቀረበ አጭር ማብራሪያ

#በጋብቻ-ውስጥ-የግልና-የጋራ-ንብረት-በኢፌዲሪ-የቤተሰብ-ህግ| #Common-Property-of-Spouses| #Ethiopian-Revised-Family-Code

#በጋብቻ-ውስጥ-የግልና-የጋራ-ንብረት-በኢፌዲሪ-የቤተሰብ-ህግ| #Common-Property-of-Spouses| #Ethiopian-Revised-Family-Code

Бехтерева раскрыла, что УБИВАЕТ мозг БЫСТРЕЕ алкоголя! УЧЁНЫЕ СКРЫВАЛИ 40 ЛЕТ!

Бехтерева раскрыла, что УБИВАЕТ мозг БЫСТРЕЕ алкоголя! УЧЁНЫЕ СКРЫВАЛИ 40 ЛЕТ!

ከትዳር በፊት መደረግ የሌለበት 5 ነገሮች - | Gabcha Tube | ጋብቻ ቲዩብ |

ከትዳር በፊት መደረግ የሌለበት 5 ነገሮች - | Gabcha Tube | ጋብቻ ቲዩብ |

አምስቱ  የጋብቻ ትዕዛዛት [The Five Commandments of Marriage] by Ashu Tefera

አምስቱ የጋብቻ ትዕዛዛት [The Five Commandments of Marriage] by Ashu Tefera

ከጋብቻ በፊት የተገኘ ንብረት የግል ይባልልኝ አቤቱታ አቀራረብ | Personal property

ከጋብቻ በፊት የተገኘ ንብረት የግል ይባልልኝ አቤቱታ አቀራረብ | Personal property

የዉርስ ህግ/የሰበር ዉሳኔ የዉርስ ጉዳይ ላይ የወራሽነት ማስረጃና የይርጋ ጉዳይ/Ethiopia succession law

የዉርስ ህግ/የሰበር ዉሳኔ የዉርስ ጉዳይ ላይ የወራሽነት ማስረጃና የይርጋ ጉዳይ/Ethiopia succession law

Кто остановит Трампа? Совет мира. Давление на ЕС. Роль НАТО. Иран. Максим Шевченко: Особое мнение

Кто остановит Трампа? Совет мира. Давление на ЕС. Роль НАТО. Иран. Максим Шевченко: Особое мнение

ከጋብቻ በፊት የግል ንብረት እንዴት ማስመዝገብ ትችላላችሁ? በውልና ማስረጃ የሚያስፈልጉ ሰነዶች‼ #Seifuonebs #donkeytube #fetadaily

ከጋብቻ በፊት የግል ንብረት እንዴት ማስመዝገብ ትችላላችሁ? በውልና ማስረጃ የሚያስፈልጉ ሰነዶች‼ #Seifuonebs #donkeytube #fetadaily

© 2025 dtub. Все права защищены.



  • Контакты
  • О нас
  • Политика конфиденциальности



Контакты для правообладателей: infodtube@gmail.com