ተወኩል እና ኢስቲኻራ | ቢስሚከ ነሕያ | ኸሚስ ምሽት ክፍል 239 Khemis Mishit Ep. 239
Автор: Minber TV
Загружено: 2025-10-09
Просмотров: 23266
እንዲህ እንደዛሬው ባለ ቀን፤ ለይሉ ጁምዓ ሲሆን አየሩ በሶለዋት ይታወዳል። የቤተሰብ ዚያራውና የወዳጅ ዘመድ አብሮነቱም በምሽቱ ይናኛል። ተነፋፍቆ የተገናኘ ቤተሰብ በዚያራ ደምቆ የልብ የልቡን ሲያወጋ ይቆይና፤ ከዒሻ ሰላት መልስ በየሳምንቱ አዳዲስ ታሪኮችና ለሩህ ስንቅና ቀለብ የሚያቀብሉ መሰናዶዎች የሚቀርቡበትን ተወዳጅ ፕሮግራም ለማየት በአንድ ልቡ በሚንበር ዙሪያ ይሰበሰባል።
"ኸሚስ ምሽት" ታዳጊዎች፣ ወጣቶች፣ ጎልማሶችና አረጋዊያን በጋራ ተሰባስበው፣ በዋናነት በሸይኻችን ለዛ ያለው ትምህርትና ወግ እየተዝናኑ ዕውቀትን የሚቀስሙበት፤ በኡስታዝ በድር ለሕይወት ቅርብ በሆኑ ኢማናዊ ጉዳዮችና ጥልቅ ትንታኔዎች መንፈሳዊ ከፍታን ለመጎናፀፍ የሚታትሩበት ደማቅ መሰናዶ ነው።
እንደ ጣቢያ ሚዛናዊ አመለካከት እንዲጎለብት፣ ኡማችን ሆደ ሰፊነትን ተላብሶ በኅብረት እንዲቆምና፤ በእስልምና የተጋመደ ጠንካራ ወንድማማችነቱን ምንግዜም እንዲያፀና ያለመታከት ስንተጋ ቆይተናል።
ይህ የኛ ራዕይና ተልዕኮ ነው። በዚህ ለዓላማ በሚደረግ ታላቅ ጉዞ ውስጥ መንገዱ ድካም አያጣውምና፤ አቅም ሲያንሰን እያበረታችሁ፣ ስንጠነክር "ወፌ ቆመች" እያላችሁ አቅማችንን ላጎለበታችሁ ሁሉ፤ አብራችሁን ስለነበራችሁ እጅግ በጣም እናመሰግናለን።
እንደ ቤተሰብ ያቀራረበን "ኸሚስ ምሽታችን" የበለጠ እንዲፈካ ከኛ ጋር ለከረማችሁ በመላው ዓለም የምትገኙ ተመልካቾችና አጋር ተቋማት ሁሉ በድጋሚ የከበረ ምስጋናችንን እናቀርባለን። ነገም ወደ ግባችን የሚደረገው ግስጋሴና ጉዟችን ይቀጥላል!!! በርግጠኝነት የናንተም አብሮነት እንዲሁ!!!
#ለይሉ_ጁምዓ_ነው!
#ፕሮግራሙ_ደግሞ_ኸሚስ_ምሽት!
ሚንበር ቲቪ!
በሚዛናዊ ዕይታ ... ዳግም ወደ ከፍታ!!
#MinberTV
#ሚንበር_ቲቪ
#5Years
#MinberTV5thYearAnniversary
Copyright @MinberTV
👨👩👧👦 Join Minber Family 🔗 https://t.me/Minber_Merkuz_Discuss
★★★★★
የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ሊንኮች👇🏽 ይወዳጁን 👍🏽 ያጋሩ ⤴️
📍YouTube 👉 / @minbertv1
📍Facebook👉 / minbertv1
📍Telegram👉 https://t.me/minbertv
📍TikTok 👉 / minber_tv
📍Instagram 👉 / minbertv
📍X / Twitter 👉 / minbertv
📍Website 👉 https://www.minbertv.com
#MinberTV
#ሚንበር_ቲቪ
#5Years
#MinberTV5thYearAnniversary
ዕለተ ሐሙስ መስከረም 22 - 2018 | ረቢዑ ሣኒ 10 - 1447
★ ★ ★
EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ!
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: