Dess - Birr - ደስ - ብር - New Ethiopian Music 2024 - ( Official Music Video)
Автор: Dess ደስ
Загружено: 2024-09-03
Просмотров: 75721
ብር - ደስ
ግጥም ዜማ - ደስ
ፕሮዲውሰር - ስሞል አክስ ሪከርድስ
የሙዚቃ አሬንጅመንት - ኤርሚያስ በዛብህ
ሚክስና ማስተሪንግ - ያምሉ ሞላ
ሲኒማቶግራፊ ኤዲቲንግ እና ከለር - ፀጋዬ ደስታ (ዋሌ ፊልምስ)
ግጥም - ብር
አጥተህ ነጥተህ ኑሮ ከብዶህ ወዳጅ እንዳታጣ
በፀሀይ እንዳትሰለፍ ታክሲ እስኪመጣ
ኪራይ ደረሰ ደሞዜ መቼ መጣ እንዳትል
ሁሉን እረስተህ ታረቅ ተሰለፍ ለብር
እውቀት ተሰጥዖ ቢኖርህ ብትሆን መላ
ሁሉ ከንቱ ነው እመነኝ ኪስህ ካልሞላ
መሄጃ የለም በባዶ መንገድ ቢሰፋ
እግር ብር ነው ሳይኖርህ ተወው አትልፋ
ፍቅር ለሽያጭ ትዳር ከተማ ወጥቷል
በከፈለ ነው መውደድ በነፃ ቀርቶል
ወልዶ ማስተማር ለፍሬ መዐረግ ማብቃት
ታሞ መታከም አይቻል እንኳንስ ምቾት
ብር ብር ብር ብር ብር ብር
ቁልፍ መፍቻ ነው ለሁሉ ነገር
በአለም ለመዋል ሰው እየመሰልክ
ገንዘብን ስራ ከሁሉ ፈጥነክ
ገንዘብን ስራ ገንዘብን ገንዘብን ስራ
ሁሉ በሽነው ያንተ ነው ኪስህ ሲሞላ
ገንዘብን ስራ ገንዘብን ገንዘብን ስራ
አለም ያንተ ነው ኪስህ ሲሞላ
ብር ብር ብር ብር
ንዋይ ለምቾት ለሁሉ ነገር
በአለም ለመዋል ሰው እየመሰልክ
ገንዘብን ስራ ከሁሉ ፈጥነክ
ገንዘብ ከሌለህ ምንም በእጅህ የለም
በከፈለ ነው አንዲህ ናት እብድ ናት አለም
ወርቅ አልማዝህን በአንገትህ አንጠልጥለህ ዙር
ድንጋዩ በልጧል ዘንድሮ ከሰው ልጅ ክብር
ጥሪትን ቋጥር ቤትህን በድንጋይ ስራ
ከአለም ተጋፋ ተጣላ ኪስህ እንዲሞላ
ነገ ነገ በል ለዛሬ ሌላ እንዳትሰማ
ደልቶህ እንድትኖር ይህ አለም ካንተ እንዲስማማ
ብር ብር ብር ብር ብር ብር
ቁልፍ መፍቻ ነው ለሁሉ ነገር
በአለም ለመዋል ሰው እየመሰልክ
ገንዘብን ስራ ከሁሉ ፈጥነክ
ገንዘብን ስራ ገንዘብን ገንዘብን ስራ
ሁሉ በሽነው ያንተ ነው ኪስህ ሲሞላ
ገንዘብን ስራ ገንዘብን ገንዘብን ስራ
አለም ያንተ ነው ኪስህ ሲሞላ
እምነት ደካክሞ ከሰው ልብ ተሸርሽሮ
እውነት ጠፍቶ ተረስቶ የሀጥያት ስር ዛሬ ከብሮ
አይኔ እያየ ህይወትን ኖሬ አስተውዬ
እንዴት አልመክርህ ገንዘብን ብርን ስራ ብዬ
አልሞተ አልገደለም ሰው ንዋይ አፍቅሮ
እራሱን አልሸጠም ከክብሩ ዝቅ ብሎ
ነብይ ሰባኪው በእግዜር ስም አታሎ ፎግሮ
ቀጥፎ የሚበላበት አይደል እንዴ ዘንድሮ
ሽማግሌው ቀሎ የሰው ሚስት በንዋይ ሲቀማ
ባለስልጣኑ ሀገሩን ሊሸጥ ሲሮጥ ሲያስማማ
በጎ ሊሰራ ቢኒያም ቆሞ ይለምናል
የደሀን እንባ ሌላው ሰርቆ ደልቶት ይኖራል
ስለዚህ ስራ አግኝ በርትተህ ጠንክረህ
ባይተርፍህ እዳ አትሁን ተገኝ እራስህን ችለህ
ቢያንስ ክፉ ብቻ ጠቅልሎ ሁሉን አይያዘው
ሀብታም ሁንና ለግስ ለአበበች ጎበና ስጠው
አትገረም አትደነቅ ብር ገንዘብ በማለቴ
የአለም እውነት ነው እንጂ ይህ አይደለም እምነቴ
ሰው እራሱን ቢያውቅ ባይገዛው የሰራው ነገር
ለከት ቢኖረው ምኞቱ ምነኛ ደስ ይለኝ ነበር
#ethiopianmusic #Dess #hiphop #ethiopianmusic2024 #amharicmusic #music #musica #musicvideo #artist #ethiopianartist #ethiopia #ethiopianmusic #ethiopian #habesha #addisababa #eritrean #ethio #habeshastyle #africa #ethiopians #ethiopianmusic #addisabeba #amharic #love #african #ethiopianmusic #ethiopianmovie #habsha #ethiopia🇪🇹 #ethiopiamusic🇪🇹 #ethiopia🇪🇹 #ethiopiamusic🇪🇹👍🏾 #culture #habshatiktok #habsselfie #jamaica #facebook #tiktokethiopia #onelove❤️ #ኢትዮጵያዬ💚💛❤ #ሀበሻ #loveyou #ethiopianculture #habesha #blakestar #brothers #habshaartist #habshamusic #cultura #ethiopianmusic #Ethiopian #Music #ethiopianmusic #amharicmusic #newmusic #ኢትዮጵያ_ሙዚቃ, #ethiopianclassicalmusic ndrama
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: