Creamy Pesto Sauce ክሪሚ ፔስቶ ሶስ
Автор: Melegna | መለኛ
Загружено: 2025-10-16
Просмотров: 3569
ይህ ምግብ ውድ እና አድካሚ ሊመስል ይችላል ነገር ግን ምግቡ በጣም ቀላል እና ትንሽ ወጪ የሚጠይቅ የምግብ አይነት ነው ፡፡ ከተለያዩ የፓስታ ዘር ምግቦችጋር ቀላቅላችሁ መመገብ ትችላላችሁ ፡፡
ሶሱን ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉ ግብዓቶች አይነት እና መጠን
የውጪውን የቤዝል ቅጠል
8 ፍሬ ነጭ ሽንኩርት
ግማሽ ኩባያ ጨዋማ ለውዝ
ነጭ ሽንኩርቱ እና ለውዙን የተሻለ ጠዓም እና ቃና እንዲኖረው በመጥበሻ በመካከለኛ ሙቀት ሞቅ ሞቅ ማድረግ አለባችሁ
ግማሽ ኩባያ ፕሮቮሎኔ ወይም ፐርሜዢያን ቺዝ
የምትፈልጉን ያህል የዌራ ዘይት
የዌራ ዘይት ከሌላችሁ ሌሎች የዘይት አይነቶችን ተጠቀሙ የዌራውን ከተጠቀማችሁ የተሻለ ጠዓም ታገኛላችሁ
ትንሽ ጨው ቀምሳችሁ መጨመር
አበሳሰል
መጥበሻ ላይ የገበታቂቤ በዝቅተና ሙቀት ሞቅ አድርጋችሁ ሶስን ከፓስታ ውሃ ጋር በመጨመር ማላላት
ፔስቶ ሶሱን ከተለያዩ የፓስታ ዘር ምግቦች ጋር አብራችሁ ቀላቅላችሁ ማብሰል ትችላላችሁ
አቀማመጥ
ፔስቶ ሶሱን ማቆየት ከፈለጋችሁ በምሳ እቃ ገልብጣችሁ ማቀዝቀዣ ቤት ውስጥ በረዶ ክፍል ውስጥ ማቆየት
እንደ አማራጭ በረዶ መስሪያ ላይ ቀንሳችሁ በረዶ አስይዛችሁ ማስቀመጥ ትችላላችሁ
ማባያ
በገበታ ቂቤ እና በነጭ ሽንኩርት የተጠበሰ ዳቦ
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: