🏠 የG+1 የግንባታ ወጪ | እቃ፣ እጅ ዋጋ ፣ማሺን ኪራይ እና ልዩ ልዩ ወጪዎች በዝርዝር | ታህሳስ 2018 – አዲስ አበባ
Автор: YG's CBD
Загружено: 2025-12-26
Просмотров: 6495
ስለ ጂ ፕላስ ዋን ቤት ግንባታ ወጪ 5 ሰዎችን ቢጠይቁ በሚያስገርም ደረጃ የተለያዩ 5 መልሶችን ሊያገኙ ይችላሉ! ታዲያ የትኛውን ግምት ትክክል ነው ብለው ይወስዳሉ? ባለፈው አመት ቤት አሰርቶ የሚያውቅ ዘመድዎን? የህንፃ ግንባታ ኮንትራከተር የሚያቀርበውን ዋጋ? ወይስ በሩቅ የሚያውቋት መሀንዲስ የሰጠችዎትን ፈጣን ግምት?
ግማሹ ሰው የሚነግረን መረጃ ከተሰራ ቆየት ያለ ቤትን መነሻ አድርጎ ሊሆን ይችላል እና የወቅቱን ዋጋ ላይወክል ይችላል፡፡ እንዲሁም የግንባታ ሳይት ርቀት፣ የአፈር አይነት፣ የሰራተኛ ክፍያ፣ የአሸዋ እና የድንጋይ ዋጋ ከሰፈር ሰፈር እንደሚለያይ የታወቀ ነው።
ከዚህ ባለፈ የቤቱ ስፋት፣ ዲዛይን እና የፊኒሺንግ ምርጫዎች በግንባታ ወጪ ላይ ያላቸውን ተፅእኖ ካላካተተ ግምት ትክክል አይሆንም። በአጠቃላይ በሀገራችን ያለው ደካማ የወጪ አመዘጋገብ ባህል እና የግልፅነት እጥረት ትክክለኛ ዋጋ ማግኘትን አዳጋች ያደርገዋል።
ስለዚህ እነዚህን ሁሉ ሁኔታዎች ግንዛቤ ውስጥ ባካተተ መልኩ በሶፍትዌር የታገዘ የግንባታ ግምት መስራት ተመራጭ ይሆናል።
በዚህ ቪዲዮ ዋይ ጂስ ሲቢዲ ፕሮግራምን በመጠቀም 104 ካሬ ስፋት ያለውን ጂ ፕላስ ዋን ቤት ከፋውንዴሽን ጀምሮ እስከ ጣርያ እና ብሎኬት ስራ ድረስ የሚያስፈልገውን ዝርዝር ወጪ እናዘጋጃለን። ግንባታው ደልዳላ ሳይት ላይ እና ኖርማል አፈር ላይ እንደሚካሄድ ታሳቢ ተደርጎ የታህሳስ 2018 ዓ.ም የአዲስ አበባ የግንባታ ግብዓት ዋጋ ተጠቅመናል።
ዝግጅቱ በአራት ክፍሎች የተከፋፈለ ሲሆን፡
• ፋውንዴሽን
• ከመሬት በላይ የኮንክሪት ስራ
• የጣርያ እና የብሎኬት ስራ
• አጠቃላይ የወጪ ድምር
ግምቱ የማቴርያል አይነት፣ ብዛት እና ዋጋ፣ የእጅ ዋጋ፣ የማሺን ኪራይ እና የአስተዳደር ወጪዎችን ያካተተ ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር ሆነው የሚያሰሩ ሰዎች ፕሮጀክታቸውን ለመከታተል መነሻ ሃሳብ እንዲያገኙበት ይረዳል።
አድራሻችን ለቴሌግራም መልእክት https://t.me/CBDReg
ኢ ሜይል YGsCBD2015@gmail.com
Getting reliable G+1 construction cost figures in Addis Ababa is difficult — ask five people and you’ll likely get five different answers.
In this video, a software-assisted, assumption-based cost estimate is prepared for a 104 m² G+1 building, covering construction from foundation up to roofing and blockwork.
The estimate is based on Addis Ababa material and labor prices, with clearly stated site, soil, and design assumptions.
This video is intended for homeowners, self-builders, and diaspora clients who want a realistic understanding of construction costs before budgeting, hiring contractors, or supervising projects remotely.
#GPlusOne
#GPlusOneConstruction
#ConstructionCostEthiopia
#HouseConstructionAddisAbaba
#BuildingCostAddisAbaba
#ConstructionCostBreakdown
#EthiopianConstruction
#HomeBuildingEthiopia
#YGsCBD
#2merkato Construction #JijiEthiopia, #constructioninethiopia # NuroBesheger, #5GTube, #ConstructionTendersEthiopia, #ConstructionMaterialCostEthiopia, #MixedUseBuilding,#CondominiumEthiopia, #ቆሮቆርብሎኬትቤት, #ሰርቪስቤት,፣ #ቪላቤት, #ዘመናዊቤት, #G+1, #G+2, #G+3, #G+4, #የንግድ ሱቅ,#RealEstateEthiopia
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: