Yenegeye Dimket | የነገዬ ድምቀት| Soreti Moges | mp3
Автор: Soreti Moges
Загружено: 2021-10-18
Просмотров: 7702
የማለዳዋን ፀሀይ ጠብቆ
ሁሉ ይሮጣል ጎጆውን ለቆ
አንዱን ሲያነሳ ደሞ ሌላውን ሲጥል
ይህን ሲያዋድድ ያንን ሲያጣጥል
እዚህ የሰራውን እዛጋ ሲያፈርሰው
እንዳልነበረ ሲደረምሰው
ይህ ሁሉ ድካም የሰው ልጅ እሩጫው
ነገን የተሸለ መልካም ለማድረግ ነው
የኔ ነገ ግን መልካም የሚሆነው
አንተን በማወቅ በማልፈው ዛሬ ነው
እንኳን ከነገ ከአሁን ትቀድማለህ
ከእስትንፋሴ ይልቅ አንተ አዎ አንተ ታስፈልገኛለህ
ኢየሱስ አንተ ነህ የነገዬ ውበት
ኢየሱስ አንተ ነህ የዘመኔ ድምቀት
አይደለም ብዙ እሩጫዬ
አይደለም ብዙ ድካሜ
አይደለም መውጣት መውረዴ
አይደለም ማግኘት ማጣቴ
አለም እለት እለት ታሳይ ትሰጥ አላት
አንተን ተጠልለው በንቀት ካልሸኟት
ነፍስን መልሶ በእረፍት አሰማሪ
ከአንድ ከአንተ በቀር ማነው ዘላለም አኗሪ
Доступные форматы для скачивания:
Скачать видео mp4
-
Информация по загрузке: